«በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ይስፈን» ኢሶዴፓ | ኢትዮጵያ | DW | 09.10.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

«በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ይስፈን» ኢሶዴፓ

በኢትዮጵያ በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸሙ ያሉት አሰቃቂ ጥቃቶች በአስቸኳይ ሊገቱ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ  «ኢሶዴፓ» መግለጫ ሰጠ። በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ስለ ሠላም መስበካቸዉ ጥሩ ቢሆንም የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጠንክረዉ መሥራት እንዳለባቸው ተናግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:46 ደቂቃ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጠንክረዉ መሥራት እንዳለባቸው

ባለፉት ዓመታት ዜጎች  በብሔር ብሔረሰብ  ማንነታቸው  ምክንያት በተለያዩ አከባቢዎች በደረሱባቸው ጥቃቶች  ከመኖሪያቸውና ከሥራ ቦታዎቻቸው ተፈናቅለው በገዛ ሀገራቸው ለስደትና ለእንግልት ሲዳረጉ መቆየታቸውን መግለጫዉ አስታውቆ አሁንም ሁኔታዉ እየተባባሰ መምጣቱን አመልክቷል። «ኢሶዴፓ» እንደዚህ አይነቶቹ ጥቃቶች እንዲቆሙና የዜጎች ሰላምና ደህንነት የሚረጋገጥበት እርምጃዎች በመንግሥት በኩል እንዲወሰዱ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ የቆየ ቢሆንም እስከ አሁን ችግሮቹ ከመባባሳቸው በስተቀር ተጨባጭ መፍትሔ ሲሰጥላቸው አልታየም ብሏል። ፓርቲዉ ለ «DW» በሰጠዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ስለ ሠላም መስበካቸዉ ጥሩ ቢሆንም የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ጠንክረዉ መሥራት እንዳለባቸው ተናግሯል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረግዚአብሔር  ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል። 


ዮሐንስ ገብረግዚአብሔር  
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic