በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ዉይይት | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ዉይይት

ውይይቱ ያተኮረባቸው ነጥቦች ፦ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከምርጫው በኋላ በኢትዮጵያ ላይ የያዘው አቋም እና ሚናው፣በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል በሚካሄደው ጦርነት የሰብዓዊ እርዳታ ሁኔታ እንዲሁም ገለልተኛ የሚባሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ስለ ኢትዮጵያው ጦርነት የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች የሚሉት ነበሩ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 06:21

ጀርመን በሚገኙ ድርጅቶች የተዘጋጀ የዐምደ-መረብ ውይይት


ኢትዮ በርሊን የተባለው በበርሊን የተቋቋመው የኢትዮጵያውያን ማኅበርና ለጀርመኑ የሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ ቅርበት ያለው ፍሬድሪሽ ኤበርት የተባለው ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የዐብደ መረብ ውይይት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ ዶክተር አስፋወሰን አስራተ የታሪክ ምሁር የኤኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪና የፖለቲካ ተንታኝ ወይዘሮ ማሬና ፔተር BROT FÜR DIE WELT ወይም "ዳቦ ለዓለም" የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ተጠሪ እንዲሁም ዶክተር ቶርስተን ሁተር በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምሥራቅ አፍሪቃና የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል ተጠሪ በውይይቱ ተካፍለዋል። ሌሎችም አስተያየታቸውንና ጥያቄዎቻቸውን በጽሁፍ በመላክ ተሳትፈዋል። ውይይቱ ያተኮረባቸው ነጥቦች ፦ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከምርጫው በኋላ በኢትዮጵያ ላይ የያዘው አቋም እና ሚናው፣በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል በሚካሄደው ጦርነት የሰብዓዊ እርዳታ ሁኔታ እንዲሁም ገለልተኛ የሚባሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ስለ ኢትዮጵያው ጦርነት የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች የሚሉት ነበሩ።ውይይቱን የተከታተለውን የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግረነዋል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ 
እሸቴ በቀለ 

Audios and videos on the topic