በኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት ያስከትለው የበረሃ አንበጣ | ኢትዮጵያ | DW | 21.10.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት ያስከትለው የበረሃ አንበጣ

በኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴ ኤታ በተለይ ለዶይቼ ቨለ /DW/ ፤ የገጠመን የገንዘብ እጥረት ችግር ሳይሆን የአየር ሽፋን አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች እክል ነው ብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:24

«መድኃኒት የሚረጭ የአውሮፕላን እጥረት መኖሩ»

የኢትዮጵያ መንግሥት የአንበጣ መንጋን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት አጥጋቢ አይደለም በሚል ከአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘረው ቅሬታ ተገቢ አለመሆኑን ገለፀ። በኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴ ኤታ በተለይ ለዶይቼ ቨለ /DW/ ፤ የገጠመን የገንዘብ እጥረት ችግር ሳይሆን የአየር ሽፋን አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች እክል ነው ብለዋል። ካሉት 6 አውሮፕላኖች ሁለቱ በመከስከስ አደጋ ሦስቱ ደግሞ በብልሽት ምክንያት የመከላከል አቅሙን መገደቡንም አመልክተዋል። እንዲያም ሆኖ አሁንም የአንበጣው መንጋ በሰብል ላይ የሚያደርሰውን ውድመት ለመከላከል በአውሮፕላንና  ሄሊኮችተሮች የታገዘ አሰሳና  የፀረ-አንበጣ ኬሚካል ርጭት እንዲሁም መኪናና የሰው ኃይል በማሰማራት ጭምር ርብርቡ ተጠናክሮ  መቀጠሉን ገልጸዋል። ለዚሁ ሥራ የዓለም ባንክ የሰጠው ድጋፍ ላይ የሚቀርበውን ክስም አስተባብለዋል።  የዓለም ባንክ በሃገሪቱ አምስት ክልሎች የተከሰተውን የአንበጣን መንጋ ለመከላከል ያበረከተው የድጋፍ ገንዘቡ ጠፍቷል አልያም ተመዝብሯል ተብሎ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ በቅርቡ ስለተሰራጨው መረጃም የሰሙት ነገር እንደሌለና ተዓማኒነት የጎደለው መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴ ኤታው፤ ትክክለኛ ማስረጃ ያለው ህጋዊ አቤቱታውን በግልፅ ለፍትህ አካላት ማቅረብ ይችላል ሲሉ መልስ ሰጥተዋል። 

 እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች