በኢሕአዴግ ዉኅደት አዴኃን አስተያየት  | ኢትዮጵያ | DW | 22.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በኢሕአዴግ ዉኅደት አዴኃን አስተያየት 

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የኢህአዴግ ውህደት አንድነትን እንደሚያመጣ አስታወቀ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በውህደቱ ዙሪያ አስተያየት መስጠት አልፈለገም፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:45

የኢሕአዴግ መዋሐድና አዴኃን

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የኢህአዴግ ውህደት አንድነትን እንደሚያመጣ አስታወቀ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በውህደቱ ዙሪያ አስተያየት መስጠት አልፈለገም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ወደ ውህድ ፓርቲ መምጣቱን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው፡፡ ውህደቱ የአገሪቱን እንድነት ያመጣል ብለው ከሚያምኑ የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ለ8 ዓመታት በኤርትራ የተጥቅ ትግል ሲያካሂድ ቆይቶ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው የአማራ ዴሞክራሲ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) አንዱ ነው፡፡ የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት ንቅናቄያቸው የኢሕዴግን ውህድ ፓረቲ መሆን ለአገራችን ህዝቦች አንድነት አንድ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡ ሆኖም ከዚህ በፊት እንደታየው አንዱ የበላይ አንዱ |የበታች የሆነ አሰራር መወገድ እንዳለትም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል፡፡ ውህደቱ ለሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በአስተማሪነቱ እንደሚወሰድ የሚናገሩት አቶ ተስፋሁን፣ “በአገራችን ያሉ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶችም በተናጠል ከመታገል ይልቅ በውህደት ጥንካሬያችንን አጎልብተን ብንታገል ውጤታማ ያደርገናል” ነው ያሉት፡፡ ህወሓት ውህደቱን መቃዎሙ ዴሞክራሲያዊ መብቱ መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም ከህዝብ ተቆርቋሪነት አንፃር አንዳልሆነ፣ ሆኖም ግን በውህደቱ ፓርቲ ጥንካሬ ላይ አሉታዊ ተፀዕኖ አንደሚኖረው የአዴኃን ሊቀመንበሩ አቶ ተስፋሁን አመልክተዋል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጠው፣ በመጭው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፍና በባሕር ዳር ከተማ ቋሚ ጽህፈት ቤት ያለው ድርጅት ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ  የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ውህደትን አስመልክቶ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አሰተያየት እንዲሰጥን ብንሞክርም ንቅናቄው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባደረጋው ስብሰባ የድርጅቱን ውህደት በአብላጫ ድምፅ ያጸደቀ ሲሆን ስያሜውንም ብልፅግና ፓርቲ አንዲባል ተስማምቷል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው የተደረሰበትን ስምምነት 45 አባላት ያሉትን የሕወሓት የምክር ቤት አባላት  ባላካተተው የምክርቤት ሰብሰባ ውህደቱንና ስያሜውን አጽድቋል፡፡ የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ ከትናንትና ጀምሮ በአዲስ አባባ እየተካሄደ ነው፡፡


ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

Audios and videos on the topic