በአፍጋኒስታን ሶስት የጀርመን ወታደሮች ተገደሉ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በአፍጋኒስታን ሶስት የጀርመን ወታደሮች ተገደሉ

በሰሜን አፍጋኒስታን በሚገኝ የጀርመን የጦር ሰፈር ትናንት አንድ የአፍጋኒስታን ወታደር መለዪ የለበሰ ግለሰብ ባስነሳዉ ተኩስ ሶስት የጀርመን ወታደርን ገድሎ ስድስት ወታደርን አቆሰለ።

default

በጠና ከቆሰሉት ስድስት የጀርመን ወታደሮች መካከል የሁለቱ ጤንነት ለህይወት በሚያሰጋ ሁኔታ ላይ ነዉ። በሰሜን አፍጋኒስታን ባጋላን በተሰኘዉ መንደር በሚገኘዉ የጀርመን የጦር ሰፈር ዉስጥ 500 የጀርመን ወታደሮች ሰፍረዉ ይገኛሉ። ኩንዱስ አፍጋኒስታን በሚገኘዉ የጀርመን የጦር ሰፈር ላይ በደረሰ ሌላ ጥቃት አራት የጀርመን ወታደሮች መቁሰላቸዉም ታዉቆአል። ከአንድ አመት ግድም በፊት በምስራቅ አፍጋኒስታን በቾስት ከተማ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በመኪና ላይ ባጠመደዉ ቦንብ ቢያንስ ስምንት ወታደሮችን መግደሉ የሚታወስ ነዉ። ከአዉሮጻዉያኑ 2001 አ.ም ጀምሮ እስከ ዛሪ 48 ያህል የጀርመን ወታደሮች በአፍጋኒስታን ህይወታቸዉን አጥተዋል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን