በአፍሪቃ የቻይና እና ሕንድ እንቅስቃሴ | አፍሪቃ | DW | 07.10.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በአፍሪቃ የቻይና እና ሕንድ እንቅስቃሴ

ቻይና እና ሕንድ የሚከተሉት የአፍሪቃ ፖሊሲ ፣ እንዲሁም ፣በማላዊ እና በታንዛንያ መካከል የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ ትኩረት በአፍሪቃ በስፋት የሚመለከታቸው ጉዳዮች ናቸው።

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ባለፈው ነሀሴ ወር ነበር የዩኤስ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን በአፍሪቃ ባደረጉት ጉብኝታቸው መደዳ በዳካር ሴኔጋል ባሰሙት ንግግር ላይ ሀገራቸው የተፈጥሮ ሀብት ጥቅምዋን ለማስከበር ብላ የሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲን ችላ እንደማትል በገለጹበት ጊዜ ቻይናን እና ሕንድን አስቆጥተዋል።

Secretary of State Hillary Rodham Clinton speaks at the 2012 World Food Prize laureate announcement ceremony, Tuesday, June 12, 2012, at the State Department in Washington. (Foto:Pablo Martinez Monsivais/AP/dapd)

የዩኤስ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን

ቻይናና እና ሕንድ የኤኮኖሚ ዕድገታቸውን ለማስጠበቅ እያሉ በአፍሪቃ ጋ የንግድ ካላንዳች ይሉኝታ ንግድ ያካሂዳሉ በሚል ከብዙ ጊዜ ወዲህ ይወቀሳሉ። በዚሁ አሰራራቸው ሱዳን ወይም ዚምባብዌን ከመሰሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚወገዙ ሀገራት ጋ የንግድ ትስስር ከማካሄድ ወደኋላ እንደማይሉ ነው የሚወቀሱት። ከዚሁ የንድግ ልውውት የሀገራቱ ሕዝቦች ብዙም ተጠቃሚ አይደሉም። የተፈጥሮ ሀብታቸው የሚዘረፍባቸው አፍሪቃውያን መንግሥታት በእኩልነት ለመደራደር አይችሉም። በዋስንግተን የቻይና እና ሕንድ ተልካች ተቋም ተንታኝ ሀያን ዋንግ ይህ የተለመደ ወቀሳ ስትል ል አጣጥለውታል።

« በአሁኑ ጊዜ ቻይናና ሕንድ በአፍሪቃ የሚያሰሩትን ወረት ወይም ካፒታል ስትመለከት፡ የአፍሪቃን የተፈጥሮ ሀብት ካላንዳች ክፍያ በነፃ ታገኝ ከነበረበት ለራስ መበልፀጊያ ይውል ከነበረው የቅኝ አገዛዝ ጊዜ ከነበረበት በጣም የተለየ ነው። ቻይና ከአፍሪቃ ለምታገኘው በነዳጅ ዘይት እና ለጋዝ አቅርቦት በምላሹ መንገዶችን፡ ድልድዮችን ወይም ወደቦችን፡ በተጨማሪም ሀኪም ቤቶችንና የኃይል ማመንጫ ተቋማትን ትገነባለች። ይህም ለአፍሪቃ ጥቅም ያስገኝላታል። የሕንድን ስትመለከት ደግሞ ስኬታማ የንግድ ንድፈ ሀሳቦችንና ውጤታማ ተሞክሮዎችዋን ይዛ በመሄድ የስራ ቦታዎችና ሌሎች የስራ ዕድሎች ትፈጥራለች።»

እርግጥ ብዙዎች ከበርካታ ዓመታት ወዲህ በግዙፉ የአፍሪቃ የተፈጥሮ ሀብት ተጠቃሚ የመሆን ፍላጎት አድሮባቸው፡ ዓይናቸውን ከነዳጅ ዘይቱ እና ጋዝ ጎን በወርቅ ብር፡ መዳብ፡ ብረት፡ ዩሬንየም እና አልማዝን በመሳሰሉት የአፍሪቃ ማዕድናትም ላይ ጭምር አሳርፈዋል።

የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እአአ ባለፈው ሰኔ ወር 2012 ዓም አዲሱን የሀገራቸውን የአፍሪቃ ስልት አስታዋውቀዋል። ስልቱ በተለይ የዴሞክራሲ ግንባታንና የኤኮኖሚ ዕድገትን ማበረታታቱ፡ ልማትንና ጸጥታን ማረጋጋጥ በተባሉት ዋነኛ ጉዳዮች ላይ አትኩሮዋል። በሳን አንቶንዮ የሚገኘው የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጠቢብ ቫይድሃያንታ ጉንድሉፔት ቬንካታራሙ ይህንኑ አዲሱን ስልት አሜሪካ ከአፍሪቃ ጋ ያላት ግንኙነት እየተዳከመ እንዳይሄድ የወሰደችው የመጨረሻ ሙከራ አድርገው ተመልክተውታል። እአአ በ 2011 ዓም ብቻ ቻይና ከአፍሪቃ ጋ 2012 ዓም 166 ቢልየን ዶላር የንግድ ግንኙነት በማድረግ ከዩኤስ አሜሪካ ቀድማ ዋነኛዋ የአፍሪቃ የንግድ አጋር ሆናለች።

« ዩኤስ አሜሪካ በአዲሱ ስልትዋ ባንድ በኩል በመንግሥታት ደረጃ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እንዲጠበቅ ብታሳስብም፡ በሌላ በኩል የኤኮኖሚ ግንኙነትዋን ለማራመድ በንግድ ተቋማትዋ አማካኝነት የምታካሂደው ድርድር ትልቅ ነቀፌታ አፈራርቆባታል። ዩኤስ አሜሪካ ፡ ምንም እንኳን ይህ አሰራርዋ የሰብዓዊ መብት ይዞታቸው ከተበላሹ ሀገራት ጋ አጋርነት መጀመር ማለት ቢሆንም፡ ኤክሶንን በመሳሰሉ ግዙፍ ኩባንያዎችዋ በኩል የአህጉሩን የተፈጥሮ ሀብት ማግኘት የምትችልበትን ልዩ ዘዴ ከመፍጠር ወደኋላ አላለችም። ይህም በአፍሪቃውያን አስተሳሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ አልቀረም።»

በዩኤስ አሜሪካ አንፃር፡ ይላሉ ጉንድሉፔት ቬንካታራሙ፡ ከመጀመሪያውያም የኤኮኖሚ ጥቅም የማስከበሩን ፍላጎታቸውን ያልሸሸጉት ቻይና እና ሕንድ በአህጉሩ የያዙት ገፅታ አዎንታዊ ነው።« በተለይ ሕንድ በአህጉሩ ከቻይና የተሻለ አመለካከት ነው ያተረፈችው። ይሁንና፡ በአህጉሩ ግዙፍ ካፒታል በማንቀሳቀስ ቻይና ቀዳሚውን ቦታ ይዛለች። »በወቅቱ በሕንድ እና በአፍሪቃ መካከል ያለው የንግድ መጠን 60 ቢልየን ዶላር ሲሆን፡ ሕንድ ይህንኑ መጠን እስከ 2015 ዓም ድረስ ወደ ዘጠና ከፍ ለማድረግ አቅዳለች። ከኢትዮጵያ እስከ ዩጋንዳ፡ ከናይጀሪያ እስከ ደቡብ አፍሪቃ ባሉ ሀገራት ቻይናውያኑን በመንገድ እና በባቡር ሀዲድ ግንባታ ላይ ተሰማርተው ማየት የተለመደ ሆኖዋል። በሚገባ የታቀደው የቻይና ስልት ከሀገራቱ መንግሥታት ጋ በቅርብ የተቀናጀ ከመሆኑም በላይ በብዙ ቢልየን ዶላር የሚገመት ብድርንም አብሮ በመስጠት ነው የሚሰራው። ከአፍሪቃ ጋ ያላት ግንኙነት የቅርብ ጊዜ ሳይሆን ለብዙ ዓመታት የዘለቀ ታሪክ ያለው መሆኑን ከማስታወስ ያልቦዘነችው ሕንድ በቻይና አንፃር በሚገባ ያልተዘጋጁ ታታ እና ጎድሬዥን የተባሉ፡ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ስልክ እና ሌሎች የኃይል ምንጭ ተቋማትዋን ወደ አህጉሩ በመላክ በንግዱ ዘርፍ ተፅዕኖዋን ለማስፋፋት ብትሞክርም፡ በጠበብት ግምት መሠረት ለቻይና ጠንካራ ተፎካካሪ ልትሆንባት አልቻለችም። እንደሚታወቀው፡ የሕንድ ብሔራዊ አርበኛ እና የነፃነት አባት የሆኑት ማሃታማ ጋንዲ በ 19 ኛው ምዕተ ዓመት ለተወሰኑ ዓመታት ደቡብ አፍሪቃ ይኖሩ ነበር። ከዚህ ሌላም ሕንድም ልክ እንደ ብዙዎቹ የአፍሪቃ ሀገራት በተለይም በአህጉሩ ምሥራቃዊ ከፊል እንዳሉት በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ብዙ ስቃይ አሳልፋለች። በብዙ አፍሪቃውያት ሀገራት ውስጥ ከሚገኙት የውጭ ዜጎች ውሁዳን ቡድኖች መካከል ሕንዳውያኑ ዛሬም ቢሆን ትልቁን ድርሻ ይሽፍናሉ። ከዚሁ ጎንም፡ ሕንድ የተመድ በአፍሪቃ በሚያካሂዳቸው የሰላም ተልዕኮ ውስጥ ግዙፍ ተሳትፎ ታደርጋለች፤ በዚህም የተነሳ በተመ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ መንበር ለማግኘት በጀመረችው ትረትዋ ላይ የአፍሪቃውያኑን ድጋፍ እንደምታገኝ ተስፋ ማድረጓ አልቀረም። የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ማንሞሀን ሲንግ ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ እንኳን በአፍሪቃ አራት ጊዜ ጉብኝት አድርገዋል።

በኒው ዴሊ የሚገኘው የጃማ ኢዝላሚያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ሱጂት ዱታ እንደታዘቡት፡ የተለያዩ ጥንካሬዎች ያሉዋቸው በአፍሪቃ በተለያ ዘርፎች የሚንቀሳቀሱት ሕንድና ቻይና ተቀናቃኞች አይደሉም፤ አንዱ ሌላው ያልተሰማራበትን ዘርፍ ይሸፍናል።

« ቻይና እና ሕንድ ኃይላቸውን እና ኤኮኖሚያቸውን ለማጠናከር ሳይታክቱ የሚሰሩ ሀገራት በመሆናቸው ብቻ ይመስለኛል ሁለቱን ተቀናቃኞች እንደሆኑ አድርገው ለማቅረብ ሙከራ የሚደረገው። »

ይሁን እንጂ፡ ቻይናና ሕንድም ቢሆኑ ወደፊት መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።

----------------------------------------------------------------

Lake malawi africa #33284668

የማላዊ ሐይቅ

በማላዊ እና በታንዛንያ መካከል የተፈጠረው የድንበር ግጭት አሁንም ገና እልባት አላገኘም። የታንዛንያ ባለሥልጣናት ባለፈው ሣምንት ብዙ የማላዊ አሣ አስጋሪዎችን በአከራካሪው የማላዊ ሀይቅ አቅራቢያ ካሰሩ በኋላ የማላዊ ፕሬዚደንት ጆይስ ባንዳ የተመድ ጣልቃ ገብቶ ለብዙ ጊዜ ተዳፍኖ የነበረውንና አሁን የፈነዳውን ውዝግብ እንዲያበቃ ጠይቀዋል። ታንዛንያ ክሱን አስተባብላለች። ማላዊ ለውዝግቡ መፍትሔ ለማፈላለግ ከታንዛንያ ጋ ጀምራው ከነበረው ድርድርም መውጣቷንም አስታውቃለች። ታንዛንያ በድርድሩ የገባችውን ቃል ጥሳለች በማለትም የወቀሱት ፕሬዚደንት ባንዳ ለውዝግቡ መጀመር ተጠያቂዋ ታንዛንያ መሆንዋን ገልጸዋል።

Malawian Vice-President Joyce Banda addresses a media conference in the capital Lilongwe April 7, 2012. Banda took over the running of the southern African nation on Saturday after the death of President Bingu wa Mutharika, and fears of a succession struggle receded as state institutions backed the constitutional handover. The government only officially confirmed 78-year-old Mutharika's death earlier on Saturday, two days after he had died following a heart attack. Seated on either side of Banda are the Inspector General of Police Peter Mukhito (L) and the Army Commander General Henry Odilo. REUTERS/Mabvuto Banda (MALAWI - Tags: POLITICS MILITARY)

የማላዊ ፕሬዚደንት ጆይስ ባንዳ

« ታንዛንያ ሀይቃችን በታንዛንያ ግዛት ውስጥ እንደሚገኝ የሚያሳይ አዲስ ካርታ ከጥቂት ለፈው ሣምንት አወጣች። ሁለተኛ አሣ አስጋሪዎቻችን የመታሰር ዕጣ ገትሞአቸዋል። ሦስተኛ፡ አንድ የታንዛንያ ጀልባ ሀይቃችን ላይ እንዳለም ሰምተናል። ከዚህ ሌላም፡ ጀልቦቻችን ወደ ድንበራችን አቅራቢያ ከታዩ እንደሚያፈነዱዋቸው ተነግሮናል። »

ፕሬዚደንትዋ የሁሉንንም ባይሆን የብዙውን የሀገራቸው ሕዝብ እና የተቃዋሚ ቡድኖችን ድጋፍ አግኝተዋል።

« ፕሬዚደንትዋ ጉዳዩን ለተመድ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ለማቅረብ የወሰዱት ውሳኔ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ውይይቱ እየተካሄደ ባለበት ጊዜ ታንዛንያ አዲስ ካርታ ማውጣትዋን አይተናል። »

« ጉዳዩን ወደ የተመድ መውሰድ መፍትሔ አይሆንም፡ እንዲያውም ውይይቱን ያደናቅፋል። »

የማላዊን ርምጃ መንቀፍዋቅፋለች ታንዛንያ መንግሥት ቃል አቀባይ አሳ ማምቤኔ ጉዳዩን ከፍርድ ቤት ውጭ በድርድር መፍታቱ የተሻለ ነው ይላሉ።

« በመሠረቱ ጉዳዩን በአካላዩ ፍርድ ቤት አማካኝነት ይፈታ በሚለው ላይ ከማላዊ ብንስማማም ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድ በፊት ሊፈተሹ የሚችሉ ብዙ አማራጮች አሉ የሚል ነው የኛ አቋም። »

ይሁንና ማላዊ በዚህ አካራካሪ ግዛት ነዳጅ ዘይት ለማውጣት ዕቅድዋ አእንዳላት ተሰምቶዋል። ይህ እንደትንኮሳ እንደሚታይ ነው የገለጹት።

«በዚህ የታንዛንያ ግዛት ነው ተብሎ በሚታሰበ አካባቢ የሆነ እንቅስቃሴ ከተጀመረ እንደ ትንኮሳ ስለምናየው ርምጃ እንደምንወስድ ለማላዊ አቻዎቻችን ግልጽ አድርገናል። ርምጃው ድርድርንም ጭምር ሊያጠቃልል ይችላል። ግን እንደሚታየው በዚሁ አካባቢ አንዳችም እንቅስቃሴ አልጀመሩም። »

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 07.10.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16Lwl
 • ቀን 07.10.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16Lwl