በአፍሪቃ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ትብብር፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 26.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

በአፍሪቃ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ትብብር፣

ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ለኤኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን፤ ውድድር፤ የተፈጥሮ ግዳጅ በመሰለበት ዓለም፤ ለኅልውና ጭምር አለኝታም ነው።

default

ዕውቁ ናይጀሪያዊ የኮምፒዩተር ሳይንስ ሊቅ ፊሊፕ ኤሜጋዋሊ፤ አፍሪቃ በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ በተለይ በሥነ ቴክኒክ ጠንክሮ ለመራመድ ካልጣረ ለዳግም ቅኝ አገዛዝ ቢዳረግ ላያስደንቅ እንደሚችል ነው የሚናገሩት። የአፍሪቃ ፤ የእስያና የላቲን አሜሪካ ነባር ህዝብ፣ የሰሜን አሜሪካም ቢሆን፤ በመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ፤ በተለይ አፍሪቃውያን በባርነት እስከመጋዝ የደረሱት፤ በኋላም በ 19ኛው ምዕተ -ዓመት በቅኝ ግዛት ሥር የዋሉት፣ ከኋላ ተነስተው በጥቂቱም ቢሆን በሥነ ቴክኒክ ቀድመው በተገኙ አገሮች መሆኑ የሚታበል አይደለም። እንደምሳሌም በጥቂት ሜትሮችና መቶ ሜትሮች ርቀት ተተኮሶ ሰው የሚገድለውን ነፍጥ(ጠብመንጃ)ና የዓለም ማዕዘናት አቅጣጫ አመላካችዋን መሳሪያ፣ «ኮምፓስ»ን መጥቀስ ይቻላል። ስለሆነም በየጊዜው እመርታ በሚያሳዬው የሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ ምርምር አፍሪቃውያን ተግተው ካልሠሩ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰላሰል ለማንም የሚያዳግት አይደለም።

ከዚህ ቀደም ፤ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ ም፣ ባቀርብነው ዝግጅት፤ በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ስለታቀዱ ፤ ከ 20 የማያንሱ የሂሳብናየተፈጥሮ ሳይንስ ተቋማት ፤ በተለይ ከ 8 ዓመት በፊት ስለተቋቋመው አፍሪቃ አቀፉ የኬፕታውን፣ የአፍሪቃ የሂሳብ ተቋም፣ Africana Institute of Mathematics(AIMS) ማውሳታችን ይታወስ ይሆናል። በእንዲህ ዓይነቶቹ ተቋማት አፍሪቃዊ አይንሻታይንን ማፍራት ይቻል ይሆን ?

በአንክሮ የሚቀርብ ጥያቄ ነው። በፕሪቶሪያ በሃገሬው ስያሜ በስዋኔ፤ የእስዋኔ ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ፤ ዶ/ር ማሞ ሙጬ----

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ