በአፍሪቃ የመልካም አስተዳደር ሽልማት ተሰጠ | ኢትዮጵያ | DW | 10.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በአፍሪቃ የመልካም አስተዳደር ሽልማት ተሰጠ

የቀድሞዉ የኬፕ ቨርዴ ፕሪዝደንት ፔድሮ ፔረስ በአፍሪቃ መሪዎች መልካም አስተዳደር ምክንያት የሚሰጠዉን የሞአ ኢብራሂም ሽልማትን ማግኘታቸዉ ተገጸ።

default

የቀድሞዉ የኬፕ ቨርዴ ፕሪዝደንት ፔድሮ ፔረስ

በፖርቱጋል ቅኝ ግዛት የነበረችዉን ኬፕ ቨርዴን ለአስር አመታት የመሩት እና ባለፈዉ ነሃሴ ወር ስልጣን የለቀቁት ፔረስ ለዚህ ሽልማት የበቁት አገራቸዉን ለሁለተኛ ግዜ ካስተዳደሩ በኋላ በሰላም ስልጣን በመልቀቃቸዉ መሆኑ የሞአ ኢብራሂም ሽልማት ኮሚቴ ተጠሪ ሳሌም አህመድ ሳሌም ዛሪ ለንደን ላይ ገልጸዋል። የሞአ ኢብራሂም ሽልማት አምስት ሚሊዮን ዶላር እና ከአሁን ጀምሮ እስከ ህይወት መጨረሻ በየአመቱ የሁለት መቶ ሽ ዶላር የሚያስገኝ ነዉ። የቀድሞዉ የኬፕቨርዴ ፕሪዝደንት ሽልማቱን እንዳገኙ ከተነገራቸዉ በኋላ እንደተናገሩት

"የሞአ ኢብራሂም ሽልማት የስራዪ ዘዉድ ነዉ። በህይወቴ ለሰራኋቸዉ ነገሮች ሁሉ ያገኝሁት ዋጋ ነዉ። ከሃምሳ አመታት በፊት በፖለቲካ ዉስጥ ከገባሁ ግዜ ጀምሮ ፖለቲካ ጉዳዮችን ብቻ ነዉ የፈጸምኩት። በዚህ ግዝያት ታድያ ጥሩዉን ነገር ነበር እንደ ግብ የወሰድኩት። ጥሩ ነገር ለአገሪ ልጆች፣ ጥሩዉን ነገር ለአፍሪቃዉያን፣ ጥሩዉን ነገር ለሰዉ ዘር በሙሉ"

እ.ጎ.አ 2008 አ.ም የቀድሞ የቦትስዋና ፕሪዝዳንት ፊስቱስ ሞጌ ይህንኑ ሽልማት ያገኙ ሲሆን፣ ከዝያ በኋላ ተስማሚ ተሸላሚ አፍሪቃዊ መሪ ባለመገኘቱ እስከዛሪ ሽልማቱ ሳይሰጥ መቆየቱም ተያይዞ ተገልጾአል።

አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ