በአፍሪቃ ቀንድ ያገረሸው ፖልዮ | ጤና እና አካባቢ | DW | 10.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

በአፍሪቃ ቀንድ ያገረሸው ፖልዮ

( የልጅነት ልምሻ) ፖልዮ ከምስራቅ አፍሪቃ አገሮች መጥፋቱ ሲነገር ቢቆይም ሰሞኑን የወጣው ዜና እንደሚያመላክተው ሶማሊያና ኬንያ ውስጥ መከሰቱ ተሰምቷል።

ፓልዮ በምሥራቅ እና በአፍሪቃ ቀንድ ያሉ አገሮች ያገረሸውን ፖልዮ ማስቆም መቻላቸው ተነግሮ ነበር። ይሁንና በተለይ በሶማሊያ በአሁኑ ሰዓት በሽታው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እየተነገረ ነው። ዶክተር አብረሃም ሙሉጌታ በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልጅነት ልምሻ ማጥፊያ ቡድን ኃላፊ ናቸው። ፖሊዮ በሶማሊያ ለምን መልሶ እንደታየ ምክንያቱን ገልፀውልናል።

በዓለም ላይ ፖልዮ ያልደፋባቸው ሀገሮች ተብለው የሚጠሩት ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ናቸው። ከነዚህ ሀገሮች በሽታውን ማጥፋት ያልተቻለበት ሁለት ዓበይት ምክንያቶች አሉ ይላሉ ዶክተር አብረሃም ይህንንም ያብራራሉ።

እንዲሁም በሽታው ወደ ሌሎች አጎራባች አገሮች እንዳይዛመት ምን ዓይነት ጥንቃቄ ሊደረግ ይችላል? ዶክተር አብረሃም መልስ አላቸው።

በአፍሪቃ ቀንድ በተለይ በሶማሊያ ዳግም ስለተስፋፋው የልጅነት ልምሻ(ፖሊዮ) በሽታ ዶክተር አብረሃም ሙሉጌታ የሰጡንን ሙያዊ ትንታኔ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic