በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ  | አፍሪቃ | DW | 19.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ 

የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራስልስ ላይ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪቃ ቀንድ ሶርያ ዩክሬይን እና ቬንዝዌላ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዉ ዉሳኔዎችን አሳልፈዋል።


የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራስልስ ላይ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪቃ ቀንድ ሶርያ ዩክሬይን እና ቬንዝዌላ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዉ ዉሳኔዎችን አሳልፈዋል። ሚኒስትሮቹ አምስት ዓመት ያስቆጠረዉን የለዉጥ ርምጃ ገምግመዉ ኅብረቱ አሁንም ለዩክሬይን ግዛታዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለዉን ድጋፍ በመግለፅ የተጀመሩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉና መጭዉ ምርጫም ፍትኃዊ እና ትክክለኛ እንዲሆን በማሳሰብ ኅብረቱ ድጋፉን የሚቀጥል መሆኑን አስታዉቀዋል። በሶርያ ላይ ባደረጉት ዉይይትም በቅርቡ ብራስልስ ላይ ለመምከር ስለተጠራዉ ስብሰባ ዉይይት አድርገዋል። ለሶርያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በመንግሥታቱ ድርጅት በኩል የሚደረገዉን ጥረት ኅብረቱ የሚደግፍ መሆኑንም ሚኒስትሮቹ ገልፀዉ፤የአዉሮጳ ኅብረት በሶርያ ዳግም ግንባታ ሊሳተፍ የሚችለዉ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር ብቻ መሆኑንም ሚኒስትሮቹ በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል። የአፍሪቃ ቀንድን በሚመለከት የኅብረቱ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት እና ከአካባቢዉ ሃገራት መሪዎች ጋር ያደረጉትን ዉይይት በሚመለከት የቀረበ ዘገባን አዳምጠዉ ተወያይተዋል። ሞጎሮኒ በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ሃገራት የሚታዩትን ተስፋና ተግዳሮቶች እንዲሁም ከኅብረቱ የሚጠበቁ ነገሮችን ሁሉ  በዝርዝር ተወስቶአል ።  


ገበያዉ ንጉሴ 


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሰ 
 

Audios and videos on the topic