1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚአፍሪቃ

በአፍሪቃ መሰረተ ልማት የግል ባለሐብቱ ተሳትፎ

ረቡዕ፣ መጋቢት 20 2015

ሀገራት ቀደም ብሎ በኮቪድ 19 ወረርሲኝ ከዚያም ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገርን እና ህዝብን ለማስተዳደር ብዙ ድጎማ እና ብድር ስላደረጉ ለመሰረተልማት እና ለኤሌክትሪክ ኃይል እንደከዚህ ቀደሙ መዋለንዋያቸውን ማውጣት ስለማይችሉ የግሉ ዘርፍ እንዲያግዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው

https://p.dw.com/p/4PREG
Äthiopien Addis Abeba | Dialog über Infrastrukturentwicklung in Afrika
ምስል Hana Demissie/DW

በመሰረተ ልማት ግንባታ አፍሪቃ መንግስታትና የባለሐብቶች ሚና

የአፍሪካን የመሠረተ ልማትና የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት መንግስታትና የግል ኩባንዮች በጋራ በሚሰሩበት ሥልት ላይ የተነጋገረ ስብሰባ አዲስ አባባ ዉስጥ ተደርጓል።በኣፍሪካ ምጣኔ ሀብት ኮሚሽን በተደረገዉ ስብሰባ ላይ የተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የኃይል ሚንስትሮችና ባለሙያዎች ተካፋዮች ነበሩ።

የመንግስት እና የግል አጋርነትን ለመፍጠር ታስቦ በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ ላልፉት ሶስት አመታት ሲሰራበት ቆይቶዋል ተብሎዋል።ሀገራት ቀደም ብሎ በኮቪድ 19 ወረርሲኝ ከዚያም ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገርን እና ህዝብን ለማስተዳደር  ብዙ ድጎማ እና ብድር ስላደረጉ  ለመሰረተልማት እና ለኤሌክትሪክ ኃይል እንደከዚህ ቀደሙ መዋለንዋያቸውን ማውጣት ስለማይችሉ  የግሉ ዘርፍ እንዲያግዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ለ DW የተናገሩት ኣቶ ዮሀንስ ሀይሉ በ አፍሪካ ምጣኔሀብት ኮምሺን የኢነርጂ ኤክስፐርት ናቸዉ።

ባለሐብቶቹ ለሚኒስትሮች ካቀረቧቸዉ መሰረታዊ ጥያቄዊች አለማቀፍ ተቀባይነት ያለው ሁሉም ወገን ሊገባው የሚችል የህግ ማዕቀፍ፣ የተረጋጋ ደህንነት እና ጥበቃ  እንደዚሁም ዘላቂነት ያለው አቋም ይኑር የሚሉት ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ የኢነርጂ እድገት ሚንስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ዋሊ  ኢትዮጵያ የመንግስት እና የግል አጋርነት አዋጅ አውጥታ በመስራት ላይ ነች ሲሉ ተናግረዋል። 
የአፍሪካ  መንግስታት የህዝብ ሀብትን ከባለሀብቶች  ጋር በማቀናጀት ቢሰሩ የተሻለ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ በተነገረበት በዚህ ስብሰባ ተካፋይ የሆኑት በአብዛኛው ከ ኣውሮፓ የመጡ ባለሀብቶች ናቸው።

ሐና ደምሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር