1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፋር ክልል የተከፈተው አዲስ ጥቃት

ሰኞ፣ ጥር 30 2014

ከቀናት በፊት ህወሓት አዲስ ጦርነት በከፈተባቸው መጋሌ እና ኮነባ በተባሉ ሁለት የአፋር ክልል አካባቢዎች በከባድ መሣርያ በፈፀመው ጥቃት ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/46dqa
Äthiopien Konflikt im Norden
ምስል Seyoum Getu/DW

«ሁለት ቦታዎች በህወሃት ኃይሎች ተይዘዋል»

ከቀናት በፊት ህወሓት አዲስ ጦርነት በከፈተባቸው መጋሌ እና ኮነባ በተባሉ ሁለት የአፋር ክልል አካባቢዎች በከባድ መሣርያ በፈፀመው ጥቃት ከሦስት መቶ ሺህ የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። አካባቢዎቹም በህወሃት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአፋር ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በአፋር ክልል ዳግም ያገረሸውን ጦርነት አስመልክቶ ከፌደራል መንግሥት መረጃ ለማድረግ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ የድሬደዋው ዘጋቢያችን መሳይ ተክሉ አመልክቷል። መንግሥት በሽብርኝነት የፈረጀው ህወሓት በአፋር የጀመረውን ጦርነት እንዳይስፋፋ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እየተገለፀ ባለበት በዚህ ጊዜ አዲስ ጥቃት የተከፈተባቸው ሁለት አካባቢዎች በህወሃት ታጣቂዎች መያዛቸው ተመልክቷል። 

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ