በአፋር በጎርፍ ለተጎዱ የተሰጠ እርዳታ | ኢትዮጵያ | DW | 16.02.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአፋር በጎርፍ ለተጎዱ የተሰጠ እርዳታ

ድርጅቱ እንዳስታወቀው በአካባቢው ለችግር ከተጋለጡት 25 ሺህ ከሚደርሱ ሰዎች በተለይ ሴቶች ሕፃናትና አረጋውያን በዚህ እርዳታ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቧል።

በአፋር በጎርፍ ለተጎዱ የተሰጠ እርዳታ
Deutsche Welthunger Hilfe የተባለው የጀርመን በጎ አድራጎት ድርጅት በአፋር ክልል በአኒባራ አካባቢ በቅርቡ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ክፉኛ ለተጎዱ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ ለሚውል ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ 400 ሺህ ዩሮ መደበ። በዓለም ረሃብ እንዲወገድ ጥረት የሚያደርገው ይኽው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የለገሰው ገንዘብ ለምግብ እርዳታ እንደሚውል የድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ተጠሪ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ድርጅቱ እንዳስታወቀው በአካባቢው ለችግር ከተጋለጡት 25 ሺህ ከሚደርሱ ሰዎች በተለይ ሴቶች ሕፃናትና አረጋውያን በዚህ እርዳታ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታስቧል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አዘጋጅቶታል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic