በአግባቡ ጥቅም ላይ ያልዋለው ቀርቅሃ በአማራ ክልል | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 11.03.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

በአግባቡ ጥቅም ላይ ያልዋለው ቀርቅሃ በአማራ ክልል

ቀርቅሃ በአብዛኛው በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ይበቅላል፡፡ የቆላና የደጋ ቀረከሐ በመባልም ይታወቃል፡፡ ምርቱ በአገራችን ከምግብ እቅዎች፣ ከወንበርና ከአጥር የዘለለ ጥቅም አየሰጠ እንዳልሆነ በአዊ አስተዳደር ዞን እንጅባራ ከተማ ከቀርቅሃ ባህላዊ ምርቶችን እየሰሩ የሚሸጡ ወጣቶች ለዶይቼ ቬለ አመልክተዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:34

የቀርቅሃ ምርት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አልተደገፈም

ቀርቅሃ በአብዛኛው በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ይበቅላል፡፡ የቆላና የደጋ ቀርቀሐ በመባልም ይታወቃል፡፡ ምርቱ በአገራችን ከምግብ እቅዎች፣ ከወንበርና ከአጥር የዘለለ ጥቅም አየሰጠ እንዳልሆነ በአዊ አስተዳደር ዞን እንጅባራ ከተማ ከቀርቅሃ ባህላዊ ምርቶችን እየሰሩ የሚሸጡ ወጣቶች ለዶይቼ ቬለ አመልክተዋል፡፡ ወጣቶቹ እንደሚሉት ሥራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያልተደገፈ በመሆኑ ብዙም ጥቅም እያገኙበት እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ ባለሙያዎችም ምርቱ ባግባቡ ጥቅም ላይ እንዳልዋለ ይናገራሉ።

ቀርቅሃ በሁሉም የአየር ፀባይ ባለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚበቅል ሲሆን የቆላና የደጋ ቀርቅሃ በመባል ይታወቃሉ፡፡ የቆላ ቀርቅሃ ውስጡ ድፍን ሲሆን በዋናነት የሚያገለግለው ለዘንግና ለምርኩዝ ነው፡፡ በደጋ ቀርቅሃ ላይ የ2ኛ ዲግሪቸውን የሰሩትና የደን ተመራማሪው አቶ አምሳሉ ንጋቱ እንዳብራሩት የደጋ ቀርቅሃ ውስጡ ክፍት ሆኖ አካሉ እየተሰነጠቀ በዋናነት ለመቀመጫ ወንበር፣ ለአጥር፣ ለምግብ ማቅረቢያነትና ለሌሎም አገልግሎቶች ይውላል፡፡

ሆኖም ግን የቀርቅሃ ምርቶች በቴክኖሎጂ ያልተደገፉና በባህላዊ መንገድ እየተሰሩ በመሆኑ አስፈላጊውን ጥቅም እያገኙ እንዳልሆኑ የቀርቅሃ ምርት ውጤቶችን የሚያመርቱ ወጣቶች ይናገራሉ፡፡
የቀርቅሃ ውጤቶችን በባህላዊ መንገድ ከሚያመርቱ ወጣቶች መካከል ወጣት ብርሀኑ የትዋለ ከቀርቅሃ የምግብ ጠረጴዛ፣ የአምፖል ማቀፊያ የመጽሀፈት መደርደረያዎችና ሌሎችም የቤት እቃዎች አንደሚሰሩአመልክታል፡፡

ሥራው በቴክኖሎጂ ቢታገዝ ከዚህ የተሸለ ተጠቃሚ ይሆን አንደነበርም ተናግሯል፡፡ ሌላው በዚሁ ስራ የተሰማራው ወጣት ፋንታሁን ጥሩነህ እንደሚለው ሥራው በቴክኖሎጂ ያልታገዘ በመሆኑ ምርታቸው ገዥ እያጣ አንደሆነ አመልክቷል፡፡  በ2010 ዓ ም መጨረሻ ኢትዮጵያ በካባቢ ደን ጥበቃና International Bamboo and Ratan Network በተባለ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ድጋፍ በቻይና ጉብኝት ያደረገው ወጣት ብርኃኑ እንደሚው ቤክኖሎጂ በመደገፍ ከቀርቀሀ የማይሰራ ነገር የለም ብሏል፡፡ 

አልባሳት፣ ጫማ ድልድዮች የመኪና ስፖንደና ምግብ ሆኖ ማገልገሉን እንደተመለከተ አበራርቷል፡፡ የደን ተመራማሪው አቶ አምሳሉ ንጋቱ የወጣት ብርሀኑ ሀሳብ በማጠናከር ቀርቀሀ ከ1500 በላይ ጥቅሞች አንዳሉትና ሀብቱን ባግባቡ መጠቀም እንዳልተቻለ ተናግራል፡፡ አጠቃላይ ለአገር በቀሉ ቀርቅሃ ትኩረት እንዳልተሰጠውም የደን ባለሙያው ተችተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች ሀብቱ ባግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ኃላፊነት አንዳለባቸውም ባለሙያው አስረድተዋል፡፡

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምግብና አየር ንብረት ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ደሳለው ፈንቴ የቀርቅሃ ሀብት ምንያህል እንደሆነ ጥናት መደረጉንና በአጠቃቀሙ ዙሪያ ጥናትና ምርምር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ የአዊ ብሔረሰብ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቡደን ወ/ሮ ጠጄ ወሌ አንዳሉት የቀርቅሃ ምርትን ዘመናዊ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ ብዙም አይደለም ወደፊት ግን ከአጋር አካላት ጋር የተሸለ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ቀርቅሃ በአማራ ክልል ምዕራባዊ ከባቢዎች በተለየም በምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በብዛት እንደሚገኝ የደን ተመራማሪው አቶ አምሳሉ አመልክተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን 

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

Audios and videos on the topic