በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተጀመረዉ ግጭት ወደ ወልድያ መሻገሩ  | ኢትዮጵያ | DW | 11.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተጀመረዉ ግጭት ወደ ወልድያ መሻገሩ 

ትላንት ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በወልድያ ዩኒቨርስቲ  በተማሪዎች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት የሰዉ ህይወት ማለፉንና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የወልድያ ከተማ ነዋርዎች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት፣ ለግጭቱ ምክንያት የሆነዉ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በተፈጠረው ግጭት አንድ የአማራ ክልል ተወላጅ ህይወት ማለፉ ነው። 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:12

ግጭት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ ነዋሪ ነኝ ያሉ ግን ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ ግለሰብ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት መረጃ መሰረት፣ በተማሪዎቹ መካከል ፀቡ አምስት ወይም ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር የተጀመረው። ያኔ የነበረዉን እና አሁን ዩኒቨርስቲዉ ያለበትን ሁኔታ ግለሰብ እንዲህ ገልጸውታል።

በግጭቱ ለተጎዱት ርዳታ የሚሰጠው ሆስፒታል ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት ተጎጂዎቹ በግል ሕክምና መስጫ ተቋሞች እየታከሙ እና በአሁኑ ሰዓት ግቢው በፀጥታ አካላት መከበቡን መስማታቸውንም ይኸው ግለሰብ ገልጿል።

ሌላ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የወልድያ ነዋሪ የተሽከርካር መንጃ ፍቃድ ለማዉጣት ትምህርት ላይ እንደምገኙ ተናግሮ በዩኒቬርስትዉ በተከሰዉ ግጭት ወደ ቤት እንድገቡ መታዘዛቸዉን ይናገራሉ።

ተማሪዎች ከግቢው ሸሽተው መዉጣት ቢፈልጉም ግቢው በመከበቡ እንዳልቻሉ በአዲግራት ዩኒቨርስቲ የምትማር እህት አለችኝ ያሉኝ አንድ ሌላ የወልድያ ነዋሪ ይናገራሉ።

የሁለቱም ክልል ዉስጥ ያሉት ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ሙሉ ደህንነት እንደማይሰማቸዉ አሁን በወልድያ፣ በአድግራትና በጎንደር ዩኒቨርስቲዮች ያለዉን ሁኔታ እንድህ ስሉ በዋትስኣፕ ላይ አስተያየታቸዉን ሊኮልናል።

ሌላ ግለሰብም በወትስፕ ላይ እንድ ስል አስተያየቱን አስፍረዋል፣ «አሁን የሀይማኖት አባቶች የወሎ አገረ ስብከት ጳጳስ ብጱእ አቡነ ኤርሚያስ መጠው እያወገዙ የተወሰነ መረጋጋት ታይቶበታል, አጋዚወች ደግሞ ተማሪወችን እየያዙ ጫማቸውን አስወልቀው ድብደባ ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል»።

በክልሉም ሆነ በፌዴራል እንድሁም በተምህርት ተቋሞች በኩል የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደርገነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic