በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት የተማሪ ሕይወት አለፈ | ኢትዮጵያ | DW | 10.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ ግጭት የተማሪ ሕይወት አለፈ

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ ምሽት በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት አለፈ። የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ከበደ ግጭቱ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓልን በሚያከብሩ ተማሪዎች መካከል መቀስቀሱን ተናግረዋል።

አቶ ዮሐንስ "በመበሻሸቅ የተጀመረ ነው" ያሉት ግጭት ወደ ድንጋይ መወራወር ማምራቱንም አክለው ገልጠዋል። "የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እያከበሩ የነበሩ ልጆች ሰብሰብ ብለው እየጨፈሩ ነበር። በመበሻሸቅ ነገር የተጀመረ ነው። ከዛ አንድ ሁለት ልጆች ተጣሉ እና ድንጋይ መወራወር ተጀመረ። ከዛ ነገሩ ሰፋ ሲል የጸጥታ ኃይሎች ገብተው በቁጥጥር ሥር ውሏል። በነበረው ግጭት አንድ ተማሪ ሕይወቱ አልፏል።"
አቶ ዮሐንስ በግርግሩ የተደናገጡ ወደ 100 ገደማ ተማሪዎች ቅጥር ግቢውን ለቀው ለመውጣት መጠየቃቸውን ተናግረዋል። አቶ ዮሐንስ የአገር ሽማግሌዎች፤ የሐይማኖት አባቶች እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር "አነጋግረዋቸው ልጆቹን አሳምነን ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እያደረግን ነው" ብለዋል። በግጭቱ ብሔርን ያማከለ ጥቃት ስለመፈጸሙ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ በፍጹም ሲሉ አስተባብለዋል። በማኅበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጨው መረጃም "የተጋነነ እና ሐቁን የማይገልፅ ነው" ሲሉ አጣጥለዋል። 

ተዛማጅ ዘገባዎች