በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌቶች እገዳ | ኢትዮጵያ | DW | 19.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌቶች እገዳ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ለከተማው  ሰላም  ስጋት  ናቸው  ያላቸውን  በከተማዋ  የሚንቀሳቀሱ  ማናቸውንም  የሞተር  ብስክሌቶች  ከሰኔ 30 2011 ዓ.ም  ጀምሮ  እንዳይንቀሳቀሱ  እንደሚያግድ ዛሬ አስታወቀ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:27

«ከሰኔ 30 2011ዓ,ም ተግባራዊ ይሆናል»

 የከተማው ሰላም በተረጋጋ ሁኔታ እየቀጠለ ቢሆንም በተደረገ ጥናት በህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደራጀ መንገድ የቅሚያ፣ የስርቆት እና አልፎ አልፎ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑ ነው የተገለጸው።  ለዚህም  ሰሌዳቸው አዲስ አበባ ያልሆኑ ሞተር ብስክሌቶች  ዋነኛ  የችግሩ  ምንጭ  መሆናቸውን በማመልከት ነው የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ሙሉ  በሙሉ  እንዳይንቀሳቀሱ  መታገዳቸውን ያመለከቱት። ይሁንና  ፖስተኞች ፣ ኤምባሲዎች እና  ሌሎች  የግል ተቋማት እንደገና  ፍቃድ  አውጥተው  በጥብቅ  ኃላፊነት  ሊጠቀሙ  እንደሚችሉም ተገልጿል።  በመሆኑም ባለንብረቶች  ንብረታቸውን  እንዲሰበስቡ  እና  ከከተማው  እንዲያስወጡ  ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው።

ሌላ  አማራጭ ጠፍቶ  ነው  ይህ  ውሳኔ  የተላለፈው  ለሚለውም ፤ ከንቲባው  «ሞተር ብስክሌቶች  የትራንስፖርት አማራጭ  አይደሉም»  ብለዋል።  በሌላ  በኩል  የጭነት  ተሽከርካሪዎች  ከተማዋን  እያጨናነቁ በመሆኑ  ከሰኔ 30  ጀምሮ  ማንኛውም  የመጫንና  የማውረድ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች  ከጠዋቱ  12 ሰዓት  እስከ  ምሽቱ  2 ሰዓት  እንዳይንቀሳቀሱ  መታገዳቸውን  ምክትል ከንቲባው  አመልክተዋል።
በቀጣይ  ግን  የግዙፍ  ግንባታዎች እና  የመንግሥት  ተቋማት  በልዩነት  እንደገና  ተመዝግበው እንዲንቀሳቀሱ  የሚደረግበት  ዕድል  ይኖራል  ብለዋል። የ2 ቁጥር  ሰሌዳ  ባላቸው  አነስተኛ ተሽከርካሪዎች  እና በታክሲዎች  በተመሳሳይ  እየተፈጸመ  ያለን  ዝርፊያ  እና  ወንጀል  ለመከላከል በሂደት  የምንሠራበት  ነው  ብለዋል። 

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic