1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአዲስ አበባ ነዋሪዎችን እጅግ ያሰጋው ወንጀል

እሑድ፣ ሚያዝያ 10 2013

ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ በኢትዮጵያ በተለይም በዋና ከተማ አዲስ አበባ ዘርፈ ብዙ ወንጀሎች እጅግ መበራከታቸውን ነዋሪዎች በማማረር ይገልጣሉ። ማንነታቸው ያልታወቁ በተባሉ ሰዎች ከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች አሰቃቂ ግድያዎች መፈጸማቸውም በተደጋጋሚ ይዘገባል።

https://p.dw.com/p/3s8w2
Äthiopien | Stadtansicht von Addis Abeba
ምስል Thomas Imo/photothek/imago images

አሰቃቂ ግድያዎቹ ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከተዋል

ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ በኢትዮጵያ በተለይም በዋና ከተማ አዲስ አበባ ዘርፈ ብዙ ወንጀሎች እጅግ መበራከታቸውን ነዋሪዎች በማማረር ይገልጣሉ። ማንነታቸው ያልታወቁ በተባሉ ሰዎች ከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች አሰቃቂ ግድያዎች መፈጸማቸውም በተደጋጋሚ ይዘገባል። ቤት ሰርስሮ ከመዝረፍ፣ ሰዎችን በተሽከርካሪዎች አስገድዶ ወዳልታወቀ ቦታ በመውሰድ የወንጀል ድርጊት ከመፈጸም፣ የውጭ ሃገራት ተወላጆችን ባሳተፈ መልኩ ከማጭበርበር፣ ማጅራት ከመምታት እና ኪስ ከማውለቅ ባሻገር በተለይ አሰቃቂ ግድያዎቹ ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከተዋል። ይኽን ብርቱ የማኅበረሰብ  ችግር ለመቅረፍ በሚመለከተው የመንግሥት አካል በኩል  በተለያዩ ጊዜያት ጥናት ላይ የተመሰረቱ ርምጃዎችን ለመውሰድ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ በተደጋጋሚ ይነገራል። ነዋሪዎችን እጅግ ያሳሰቡት የወንጀል ድርጊቶች ግን ከፍ ወዳለ ደረጃ መሻገራቸው ይነገራል።  ፖሊስ የመገናኛ አውታሮች ጉዳዩን አግንነውት ነው እንጂ የወንጀል ድርጊቶቹ ከቀድሞው እንደውም የቀነሱ ናቸው ይላል። ለመኾኑ በተለይ በዋና ከተማዪቱ ላይ ነዋሪዎችን ያሳሰበው የወንጀል ድርጊት መጠኑ እና አይነቱ ምን ይመስላል? የወንጀል ድርጊቶቹን ለመቀነስስ ምን ሊደረግ ይገባል? የዛሬው የእንወያይ መሰናዶዋችን የሚያጠነጥንበት ርእሰ ጉዳይ ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ