በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት | ኢትዮጵያ | DW | 21.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአውሮፕላን አደጋ ለሞቱት ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት

ፍሬድማን ሩቢን የተባለው የህግ ቢሮ እና ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ሼክስፒር ፈይሳ ለDW እንደተናገሩት ለሟች ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት ለመስጠት ተስማምተዋል።

መጋቢት 1፣2011 በረራ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ቤተሰቦች የህግ አገልግሎት ለመስጠት መንቀሳቀስ መጀመራቸውን አሜሪካን የሚገኝ አንድ የህግ ጉዳዮች ቢሮ እና አንድ ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሞያ አስታወቁ። ፍሬድማን ሩቢን የተባለው የህግ ቢሮ እና ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ሼክስፒር ፈይሳ ለDW እንደተናገሩት ለሟች ቤተሰቦች ነጻ የህግ አገልግሎት ለመስጠት ነው የተስማሙት። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።  

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

 

Audios and videos on the topic