በአቶ ዮናታን ክስ ላይ የተሰጠው ብይን | ኢትዮጵያ | DW | 04.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በአቶ ዮናታን ክስ ላይ የተሰጠው ብይን

ችሎቱ አቶ ዮናታን የተከሰሱባቸው ጽሁፎች ፣የመናገር ነጻነት ላይ የተደረጉ ክልከላዎችን እና የፀረ ሽብሩን አዋጅ 652 /2001 አንቀጽ 4 ን የሚተላለፉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:07

የፍርድ ቤት ብይን


ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዮ በተከሰሱበት የፀረ ሽብር ህግ እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ ። ችሎቱ አቶ ዮናታን የተከሰሱባቸው ጽሁፎች ፣የመናገር ነጻነት ላይ የተደረጉ ክልከላዎችን እና የፀረ ሽብሩን አዋጅ 652 /2001 አንቀጽ 4 ን የሚተላለፉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ። ፍርድ ቤቱ አቶ ዮናታን የመከላከያ ምስክሮች ይዘው እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic