በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ማማሻሻያ የተደረገባቸዉ አንቀጾች   | ኢትዮጵያ | DW | 10.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ማማሻሻያ የተደረገባቸዉ አንቀጾች  

ከትላንት ወዲይ የመከላክያ ሚንስቴር የሆኑት አቶ ስራጅ ፌጌሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ አንድ ወር በኋላ የተወሰኑት አንቀጾችን መከለስ መገደዳቸዉን ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:19 ደቂቃ

የአስቸኳይ ጊዜ መመርያ ቁጥር ሁለት

በዚህም ክለሳ አራት ክፍሎችንና ዘጠኝ አንቀፆች የያዘ የአስቸኳይ ጊዜ ርምጃ አፈፃፀም መመርያ ቁጥር ሁለት የተሰኘዉ ማዉጣት እንደተቻለም አብራርተዋል። ቀደም ብሎ የወጣዉ ክፍል አንድ መመርያ ቁጥር አንድ ዉስጥ ያሉት የትርጓሜ ችግሮችን የሚፈታ ሲሆን ክፍል ሁለት መመርያ ደግሞ «ያልተፈቀዱ የህግ አስካበር አልባሳትን ይዞ መገኘት፣ ቤት ዉስጥ ማስቀመጥ፣ አሳልፎ መስጠትና መሸጥ» ያስቀጣል የሚልለዉም በመመርያ ቁጥር ሁለት እንዲነሳ ተደርገዋል ስሉ አቶ ስራጅ ተናግረዋል።

በመመርያ ቁጥር ሁለት አንቀፅ 18 ላይ የተደነገገዉ በሐገሪቱ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ያለፈቃድ ከአዲስ አበባ ዉጪ ከአርባ ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት እንዳይጓዙ የተባለዉ ድንጋጌ መነሳቱንም ተናግረዋል።

መጀመርያ በታወጀዉ ሕግ ላይ የዲፒሎማቲክ መኅበረሰቡን ዝዉዉር የሚገድብ በመሆኑ የዲፕሎማቲክ መኅበረሰቡን አስቆጥቶ እንደነበር ይታወሳል። በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዋጁ ላይ ዴፕሎማቶች ያለፍቃድ ከ40 ኪሎሜትር መዉጣት አይችሉም ተብሎ የተደነገገዉ ኤምባስዉ ለዜጎቹ የሚገባዉን አገልግሎቶች እንዳይሰጥ በክፉ ይጎዳዋል ሲል ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል።

ኢትዮጵያ የሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲየቀድሞ አማባሳዳር የነበሩት ዴቪድ ሽን ይህ እገዳ ለመነሳቱ ምክንያት ነዉ ያሉትን ለዶቼ ቬሌ አብራርተዋል፤ «ዋናዉ ነጥብ፣ መንግስት ይህን ርምጃ ለመዉስድ ያስገደደዉ የዴፕሎማቶችን ደኅንነት ለመጠበቅ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህ በክፊል እዉነት ሊሆን ይችላል። ግን በተመሳሳይ መንግስት ዲፕሎማቶች ችግሮች ወዳሉባቸዉ ቦታዎች ሄደዉ እንዳይጎበኙና ለመንግስታቶቻቸዉ የኢትዮጵያ መንግስትን ሊያሳፍር የሚችል ዘገባን እንዳያቀርቡ ለማረጋገጥ ሲባል የተደረገ ነዉ። በተመሳሳይ ግን የኢትዮጵያ መንግስት የዉጭ ጎብኚዎችን ጉዞ አልገደበም። ይህ ተጻራሪ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። ምክንያቱም ዴፕሎማቶች ከአዲስ አበባ ዉጭ ከ40 ኪሎሜትር በዘለለ ሳያሳዉቁ ያለፈቃድ ለመንቀሳቀስ አይችሉም ተብሎ፤ ግን የዉጭ ጎብኝዎችን ያለፍቃድ መንቀሳቀስ ይችላሉ ማለት፤ መንግስት እንደሚለዉ፤ የዉጭ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ነዉ፤ ይህ አዋጅ  ከተባለዉ ጉዳይ ጋር የማይጣጣም ይመስላል።»

አዲሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መመርያ ቁጥር ሁለት ይዞ የመጣዉ ሌላ ማሻሽያ የጸጥታ አካላት በራሳቸዉ ላይ ጥቃት ሲዘነዘርባቸዉ ራሳቸዉን ለመከላከል ርምጃ መዉሰድ እንደሚችሉ ፤  በብርበራ ወይም በፍተሻ ወቅት ማንኛዉም የጝግ አስከባሪ የመስርያ ቤቱን መታወቅያ ማሳየት፣ ለምን ብርበራ እንደሚያካሄድ ምክንያቱን መስረዳት፣ ከፖሊስ ወይም ከማኅበረሰቡ በታዛቢነት እንዲሳተፉ የማድረግና ከብርበራ በፊት ወይም በኋላ የሚገኙትን  ሚስጥሮች ለመጠበቅ ጊዴታ እንዳለባቸውም አቅፎ እንደያዘ አቶ ስራጅ ፌጌሳ ተናግረዋል። 

መርጋ ዮናስ 

አዜብ ታደሰ
 

Audios and videos on the topic