«በአማራ ክልል የጤና ዘርፍ ለገጠመው ቀውስ መፍትሄው በተፋላሚዎች እጅ ነው»
ረቡዕ፣ ጥቅምት 6 2017በአማራ ክልል የጤናው ዝርፍ ችግር ላይ ነው ተብሏል።
በአማራ ክልል የሚደረገው ጦርነት በከልሉ የጤና ሥራ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ መሆኑን ምሁራን ተናገሩ። በርካታ የጤና ተቋማትና ባለሙያዎቸ ከስራ ውጪ መሆናቸውንም የአማራ ዩኒቨርስቲዎች ፎረም ባዘጋጀው ” ጦርነት ባልባቸው የክልሉ አካባቢዎቸ ሰባብአዊ ድጋፍ እንዴት ማድረስ ይቻላል” በሚል ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት ተገልጧል።
የጤና ተቋማት ሁኔታ በአማራ ክልል
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ፎረም ሴክሬታሪ ጀኔራል ዶ/ር ታፈረ መላኩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በክልሉ የነበረው ጠንካራ የህብረተሰብ የጤና አገልገሎት በአሁኑ ሰዓት በእጅጉ አሽቆልቁሏል። በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲያውም የጤና አገልግሎቱ እስከ አካቴው ተቋርጧል ነው ያሉት።
ለዚህም ምክንያቱ በክልሉ ባለው ጦርነት የሰበአዊ መብቶቸ ባለመከበራቸው እንደሆን ዶ/ር ታፈረ ገልጥዋል።
በአማራ ክልል የኤች አይቪ ስርጭትና የመድኃኒት አቅርቦት ችግር
በክልሉ ውጊያ ላይ ያሉ ኃይሎቸ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድንጋጌዎቸን አንዲያክብሩ አሳስበዋል፣ ዓለም አቀፍ ረጂ ግብረሰናይ ድርጅቶችም ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
“የግጭቱ ዋና ተዋናዮች የዓለም አቀፍ ሕጎችን እንዲያከብሩና ለስትራቴጅው ትግበራ ሙሉ ትብብር እንዲያደርጉ የበኩላችሁን ድርሻ እነድትወጡ እንጠይቃለን” ብለዋል።
በጤናው ዘርፍ ያለው ቅውስ ከፍተኛ ነው ያሉት ዶ/ር ታፈረ፣ ባለድርሻ አካላትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ጠይቀዋል።
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ተመራማሪና የህብርተስብ ጤና ፕሮፌሰር ፈንቴ አምባው የፋኖ ታጣቂዎችም ሆኑ የመንግ ሥት የጸጥታ ኃይሎች ዓለም አቀፍ የሰብ አዊ ድንጋጌዎችን አንዲጥበቁ ተማጽነዋል።
አማራ ክልል በ1ዓመት ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል
ዓለም አቀፍ ሕጎች ሊከበሩ ይገባል
የጤና አገልግሎቱ ሊድንና ሊመልስ የሚችለው ዓለም አቀፍ ህጎችና ደንቦች ሲከበሩ በመሆኑ በክልሉ በውጊያ ላይ ያሉ ሁለቱም ወገኖቸ እነኚህን ሕጎች አእንዲያከብሩና አእንዲያስከብሩ ተማጽነዋል። የጤና ባለሙያዎችም በገቡት ቃል መሰረት ሁሉንም አካል ያል አድለዎ ማገልገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አሁን ክልሉ ከደረሰበት የጤና ችገር ለመውጣት ዓለም አቀፉን ማሀበረሰብ ከጎናችን ማሰለፍ ይገባል ብለዋል።
በአማራ ክልል በፊስቱላ የሚጎዱ ሴቶች ቁጥር መጨመር
መረዳዳትና መደማመጥ አለመቻል
አንድ የውውይይት ተሳታፊ “እርስ በእርሳችን መደማምጥና መረዳዳት ባልመቻላችን ችግራችን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣለቃ ገብቶ እንዲያግዘን መደረግ አለበት” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ብችግርም ውስጥ ሆነው ባለፍው ዓመት ባለሙያዎቻቸው ለ1.5 ሚሊዮን የወባ ህሙማን ህክምና መስጠታቸውን አመልክተዋል። ከሐምሌ 2017 ዓም ውዲህ ደገሞ ከግማሽ ሚሊዮን ብላይ የወባ ታካሚዎችን መድረስ መቻሉን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ፎረምና ተባባሪ አካላት “በጦርነት አካባቢ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረስ ይቻላል” በሚል በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ምሁራንና ተባባሪ አካላት ውይይት አድርገዋል።
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ