1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የመስቀል በዓል የጦርነት ጥላ እንዳጠላ ተከብሮ ውሏል

ሰኞ፣ መስከረም 17 2014

የመስቀል በዓል በአማራ ክልል ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ባይከበርም፣ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ወቅታዊ ሁኔታው ጥላ እንዳጠላበት ተከብሯል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል እንዳለበት በሚታመንበት የግሽን ማሪያም የመስቀል በዕል ቁጥሩ በቀነሰ ምዕመናን መከበሩን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል። 

https://p.dw.com/p/40vuH
Äthiopien | Amhara Region in Artuma
ምስል Eric Lafforgue/imago images

በአማራ ክልል የጦርነት ድባብ እንዳጠላ የመስቀል በዓል ተከብሮ ውሏል

የመስቀል በዓል በአማራ ክልል ጦርነት ባለባቸው አካባቢዎች ባይከበርም፣ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ወቅታዊ ሁኔታው ጥላ እንዳጠላበት ተከብሯል፣ በየዓመቱ በርካታ ምዕመናን በሚገኙበትና እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል እንዳለበት በሚታመንበት የግሽን ማሪያም የመስቀል በዕል ቁጥሩ በቀነሰ ምዕመናን መከበሩን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል።  በመጠለያ ጣቢያ ያሉ ተፈናቃዮች የበዓል ቀን መሆኑን እንኳ ሳያውቁ ቀኑን ማሳለፋቸውን ተናግረዋል። በቅርቡ ጦርነት በተካሄደበት ምዕራብ ጎንደር ሽንፋ ከተማ ግን ከበፊቱ ባልተለየ መልኩ በዓሉ መከበሩን አንድ ከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል፡፡


ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ