1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል በዳኞች ላይ እስር እና ማዋከብ እየተፈጸመ ነው ፤ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን

ቅዳሜ፣ ጥር 3 2017

ኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን በታህሳስ ወር 2017 ዓመተ ምህረት ባወጣዉ ሪፖርት በአማራ ክልል ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ዳኞች ላይ እስርና ማዋከብ መፈፀሙን ካሰባሰበዉ መረጃና ማስረጃ ማረጋገጥ እንደቻለ አሳዉቋል ወይዘሮ እጂጋየሁ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ኗሪ ሲሆኑ በወረዳዉ ዳኛ የሆነ ወንድማቸዉና ባለቤቱ መታሰራቸዉን ይናገራሉ

https://p.dw.com/p/4p3St
Symbolbild | Justiz
ምስል fikmik/YAY Images/IMAGO

በአማራ ክልል የቀጠለው የዳኞች እስር እና ወከባ መቀጠል

የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን በታህሳስ ወር 2017 ዓመተ ምህረት ባወጣዉ ሪፖርት በአማራ ክልል ከዳኝነት ጋር በተያያዘ ዳኞች ላይ እስርና ማዋከብ መፈፀሙን ካሰባሰበዉ መረጃና ማስረጃ ማረጋገጥ እንደቻለ አሳዉቋል ወይዘሮ እጂጋየሁ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ኗሪ ሲሆኑ በወረዳዉ ዳኛ የሆነ ወንድማቸዉና ባለቤቱ መታሰራቸዉን ይናገራሉ

የዳኞች መታሰር
ወንድሜ ታሰሯል የፍርድ ቤት ዳኛ ነዉ ሚስቱም መምህር ናት ሁለቱም ታስረዋል አንድ ሴትና አንድ ወንድ ልጂ አላቸዉ የሁለቱም ደመወዝ ታግዷል  ልጆቹን የያዝኩት እኔ ነኝ እናም ምንም መፍትሄ የለም ደብረብርሀንም ወስደዋቸዉ ነበር በዚያ ሁለት ወር ቆይተዉ ፍርድቤትም ቀረቡ ፋይል ተዘግቷል ብለዉ በድጋሜ ሀሙስ ዕለተ አመጣቸዉ ይላሉ

“የዳኞች እስራት አሳስቦኛል” የአማራ ዳኞች ማህበር

በክልሉ የቀጠለዉ የዳኞች እስር

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በአባለቱ ላይ እየተስተዋለ ያለዉን የዳኞች እስር ማዋከብና ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ለሚመለከታቸዉ አካላት ማሳወቁን የሚገልፁት የማህበሩ ተወካይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አሳሳ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ዳኞችን ለማስፈታት የተደረጉ ጥረቶች ቢኖሩም አሁንም ግን እስሩ አልቆመም ብለዋል
<ያሉበትን ወረዳና እስር ቤት ለመንግስት አካላት ከዚህ ቀደም አሳዉቀናል ለክልሉ ምክር ቤትም ለርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድቤትም ጭምር በመጀመሪያ ዙር ላይ 13 ዳኞች ናቸዉ ታስረዉ የነበሩት ከዚያ በኃላ 4 ዳኞች ከአስር ቀን እስር በኃላ ተፈቱ ከዚያ ዉጭ ሌሎቹ ዘጠኝ ዳኞች ታስረዉ ነዉ የቆዮት አሁንም ከሦስት ወር በላይ እስር ላይ ነዉ የሚገኙት አንድ ዳኛ  ከዘጠኙ በቅርቡ  ቢፈታም በተጨማሪ ግን ሌሎች ዳኞች እየታሰሩ  ነዉ> ሲሉ ይናገራሉ

የአማራ ክልል የፍትህ ስርዓት ፈተናዎች

ጥያቄ ዉስጥ የገባ የዳኝነት ነፃነት

,የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ሰብሳቢ አሁን ላይ በአማራ ክልል የዳኝነት ነፃነት ጥያቄ ዉስጥ የገባ ነዉ በማለት ማህበሩ በተደጋጋሚ  የሚያነሳቸዉ ችግሮች በኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን የተረጋገጠ መሆን ችግሩ ምን ያህል የዳኝነት ስርዓቱን የሚጎዳ ለመሆኑ ማሳያ ነዉ ብለዋል
< እኛ ክልል ላይ ይህ በጣም በጎላ ደረጃ  ተጥሷል ነዉ የኛ ጥያቄ እሱ ደግሞ የተፈጠረዉ ዳኞቹ በሰጧቸዉ ዉሳኔዎች ከስራቸዉ ጋር በተገናኘ ነዉ የታሰሩት ወይም አፈፃፀምን በተመለከተ ኃላፊዎች አላስፈፅምም ሲሉ እነሱን እንዲታሰሩ ያዛሉ አንተ እኔን አታስረኝም ብሎ ፖሊስ ልኮ ዳኛዉ እንዲታሰር ያደርጋል ስለዚህ በሰሯቸዉ ስራዎች ምክንያት ዳኞች እስከታሰሩና እስከተንገላቱ ድረስ የዳኝነት ነፃነት አሁን በክልሉ አለ ብሎ ማሰብ አዳጋች ነዉ የሚሆነዉ > በማለት ይናገራሉ።

በአማራ ክልል አሳሳቢው የነባር ዳኞች ስራ መልቀቅ

የክልሉ ዳኞች ማህበር ቀጣይ እርምጃ

በቀጣይ አሁን የታሰሩ ዳኞች ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር እየተሰሩ በሚገኙ ስራዎች ይፈታሉ የሚል ተስፋ ማህበሩ እንዳለዉ አቶ ብርሃኑ አሳሳ  ገልፀዉ ይህ ሆኖ የማይገኝ ከሆነ ግን ሌሎች እርምጃዎችን እናጤናለን ይላሉ
<እነኝህ የታሰሩ ዳኞች ጠቅላይ ፍርድቤቱ በሚሄድበት እርቀት ይፈታሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ይህ የሚቀጥልና የማይሆን ከሆነ ቁጭ ብለን ተመካክረን የምንወስዳቸዉ እርምጃዎች ይኖራሉ የዳኝነት ነፃነትን ገለልተኝነትን ጥያቄ ዉስጥ የማይጥሉ እርምጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ>
በአማራ ክልል ከዳኞች እስር ጋር በተያያዘም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሀሳቡን እንዲያጋራን ፕሬዝደንቱን ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።

ኢሳያስ ገላው 

ታምራት ዲንሳ