በአማራ ክልል ሥራ የጀመሩ ሁለት የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከላት | ኢትዮጵያ | DW | 05.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

 በአማራ ክልል ሥራ የጀመሩ ሁለት የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከላት

ካባሕር ዳሩ ሌላ የደሴ የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከልም ሥራ መጀመሩን የአማራ ክልል አስታውቋል። እነዚሁ በመንግሥት እና በለጋሽ ድርጅቶች ትብብር የተገነቡት ሁለት የኦክስጂን ማመረቻ ማዕከላት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣባቸው ተገልጿል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:03

የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከላት በባህርዳር እና በደሴ

መሠረታዊ መድሐኒት የሚባለው ኦክስጂን በየሆስፒታሉ በቀላሉ እንዲገኝ አቅርቦቱም ዘላቂ እና አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሠራ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በባሕር ዳር የኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል ትናንት በተመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። ካባሕር ዳሩ ሌላ የደሴ የኦክስጂን ማምረቻ ማዕከልም ሥራ መጀመሩን የአማራ ክልል አስታውቋል። እነዚሁ በመንግሥት እና በለጋሽ ድርጅቶች ትብብር የተገነቡት ሁለት የኦክስጂን ማመረቻ ማዕከላት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣባቸው ተገልጿል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሀገሪቱ በኦክስጂን አቅርቦት እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ ተናግረዋል። ዝርዝሩን ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ልኮልናል።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ  
 

Audios and videos on the topic