1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች

ዓርብ፣ መጋቢት 2 2014

ኢሰመኮ በአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ ያደረገውን ምርምራ ዘገባ ዛሬ መጋቢት 2፤ 2014 ይፋ አደረገ። በ153 ገጾች በተዘጋጀው የምርመራ ሪፖርት ኮሚሽኑ በአማራና በአፋር ክልል አካባቢዎች ባሰማራው የሰብዓዊ መብቶች የምርመራ ቡድን የደረሰባቸውን ግኝቶች የሚያሳይ ነዉ። 

https://p.dw.com/p/48MjN
ምስል Solomon Muchie/DW

በጦርነቱ ተሳታፊ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች በርካታ ሲቪል ሰዎች ሞተዋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ ጥሰቶች ላይ ያደረገውን ምርምራ ዘገባ ዛሬ መጋቢት 2፤ 2014 ይፋ አደረገ። በ153 ገጾች በተዘጋጀው የምርመራ ሪፖርት ኮሚሽኑ ከዚህ ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ በአማራና በአፋር ክልል አካባቢዎች ባሰማራው የሰብዓዊ መብቶች የምርመራ ቡድን የደረሰባቸውን ግኝቶች የሚያሳይ ነዉ። በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በአብዛኛው ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው የከተማ እና ገጠራማ አካባቢዎች መካሄዱን  የሚያሳየዉ የኮሚሽኑ የምርመራ ዘገባ፤ በጦርነቱ ተሳታፊ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲቪል ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ለአካል እና ለስነ ልቦና ጉዳት መዳረጋቸውን እንዲሁም ጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው በምርመራ ሪፖርቱ ተገልጿል። 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ