በአለም አንጋፋዉ የአየር ማረፍያ ለጡረታ | ባህል | DW | 04.11.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

በአለም አንጋፋዉ የአየር ማረፍያ ለጡረታ

በአለም ረጅም እድሜ ያለዉ የአዉሮፕላን ማረፍያ በጀርመን እንደነበር ያዉቃሉ? ሰማንያ አምስት አመቱን የያዘዉ በበርሊን የሚገኘዉ እና በአለም ረጅም እድሜን ያስቆጠረዉ የአየር ጣብያ የመጨረሻዉን የአየር በረራ ባለፈዉ ሳምንት አስተናግዶ

default

በአለም ጥንታዉዊ የተሰኘዉ የጀርመኑ የመጀመርያ የአየር ጣብያ በበርሊን እንብርት ላይ ቢገኝም የዛሪ ሰማንያ አምስት አመት ማለት እ.አ 1923 አ.ም ግድም በርሊን ከተማ እንዲ እንደ አሁኑ ሳይሰፋ ከከተማዉ ወጣ ብሎ ነበር የሚገኘዉ

የዛሪ ሰማንያ አመት ግድም ታሪካዊ አከፋፈት እንደተደረገለት ሁሉ የአየር ማረፍያዉ ታሪካዊ መዝግያ ተደርጎለት ለጡረታ በቅቶአል። በዛሪዉ የባህል መድረካችን ስለ በርሊኑ ቴምፕሎሆፍ የአዉሮፕላን ማረፍያ በጥቂቱ የምንዳስሰዉ ርእሳችን ይሆናል። ሌላዉ የበጋዉ ወራት አልፎ ዝናብ የበዛበት ጭጋጋማዉ የክረምቱ መንደረሪያ የሆነዉ ወራት ሲገባ በምዕራባዉያኑ ዘንድ የሚከበረዉ ሃለዊን የተሰኘዉ ጥንታዊ የሆነ ባህላዊ በአል ባለፈዉ አርብ ምሽት ተከብሮአል። የሃለዊን በአል ምንን አስመልክቶ ይከበራል? በአሉስ እንዴት ይከበራል? ጀርመናዉያንስ እንዴት ያከብሩታል? ለሚለዉ በዛሪዉ የባህል መድረካችን የሚዳስሰዉ ነዉ። ሌላዉ ባለፈዉ ቅዳሜ በዚህ በጀርመን አለ ሃይሊገን እየተባለ ስለሚጠራዉ የካቶሊካዉያን የቅዱሳን መታሰብያ ቀን ሌላዉ ዛሪ በጥቂቱ የምናየዉ ርእሳችን ነዉ ያድምጡ