በናይጀርያ አፈንጋጭ ሀገረ-ገዢዎች ግንባር ፈጠሩ | አፍሪቃ | DW | 30.11.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

በናይጀርያ አፈንጋጭ ሀገረ-ገዢዎች ግንባር ፈጠሩ

የናይጀርያ ገዥዉ ፓርቲ የህዝባዊ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በእንጊሊዘኛ አፅህሮቱ PDP አዲስ የፖለቲካ ፈተና ገጥሞታል። የገዥዉ ፓርቲ አባላት የነበሩ ሰባት ሀገረ ገዥዎች ከፓርቲያቸዉ አፈንግጠዉ፤ All Progressives Congress (APC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ከተሰኘዉ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር የጋራ ፓርቲ መስርተዋል።

እነዚህ ከገዥዉ ፓርቲ አፈንግጠዉ የወጡት ሀገረ ገዥዎች የመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲን ተቀላቀሉ ማለት፤ ሀገሪቱን ከሚመራዉ የፖለቲካ ፓርቲ በበለጠ ተቃዋሚ ፓርቲ በሀገሪቱ ምክር ቤትም ከፍተኛ አባላት ቁጥር አላዉ እንዲሁም፤ የሀገሪቱንም አብዛኛዉን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል። በእንግሊዘኛ አፅህሮቱ APC በመባል የሚታወቀዉ ዋንኛ ተቃዋሚ ፓርቲ፤ አዲሶቹ ሹማምንት ሲቀየጡት ከአፍሪቃ ትልቁ ፓርቲ መሆኑም

የፓርቲዉ መሬዎች በኩራ ይገልፃሉ። ለዚህ ፓርቲ እንቅስቃሴ ዓላማዎች መካከከል የፓርቲዉ ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት የሀገሪቱ ፕሪዚዳንት ጉድ ላክ ጆናታን በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም ዳግም እንዳይመረጡ ለማድረግም እንደሆን ተነግሮአል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የዶቼ-ቬለዉ ሳም ኦሉኮያ ከሌጎስ ያጠናቀረዉን ዘገባ እንደሚከተለዉ ይደመጣል።
የናይጀርያ ገዥ ፓርቲ የፕሬዝዳት ጆናታንን አመራር በመቃወም፤ ሰባት ሀገረ-ገዢዎችና አንድ የቀድሞ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ፤ All Progressives Congress (APC በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) ከተሰኘዉ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ጋር የጋራ ፓርቲ የተመሰረተዉ ለወራቶች ከዘለቀ ከፍተኛ ቅራኔና ሽኩቻ በኋላ ነዉ። Alle Progressive Congress ፤ ከተለያዩ የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተጨማሪም ከታዋቂዎቹ ሁለት የናይጀርያ መንግሥት ተቀናቃኞች ፤ መካከል የወጣ ፓርቲ ነዉ። የመንግስት ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በአንድ የተሰባሰቡበት በናይጀርያዉ ፖለቲካ ፓርቲ APC ፤ መርህም በመጭዉ ጎርጎረሳዊ 2015 ዓ,ም በሀገሪቱ በሚካሄደዉ ምርጫ ፕሪዚዳንት ጉድላክ ጆናታን፤ እንዳይሳተፉ ለማድረግ የተደረገ ሙከራ መሆኑም ግልፅ ነዉ። All Progressives Congress (APC ) ከተሰኘዉ የናይጀርያ መንግስት ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ቦሎ ቲኑቡ ፤ በምክር ቤት ይህ የተቃዉሞ ፓርቲ በአዲስ መልክ በመመሥረቱ ደስተኛ መሆናቸዉን ይናገራሉ፤


« በዚህ ክስተት ደስተኞች ነን። ሀገራችንን ከአንድ ቡድን ሥራ ለማስጣል እና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሟሟላት በቁርጠኝነት ተነስተናል። »
በናይጀርያ የፖለቲካ ጉዞ የAPC ፓርቲ መመስረት ናይጀርያ ወደ ዲሞክራስያዊ ሥርዓት ከተቀየረች ከ 15 ዓመታት ወዲህ ትጠቀመዉ የነበረዉን ሁሉ ታጣለች። የዚህ ተፅኖ ደግሞ ፕሪዚዳንት ጆናታን ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም ምርጫ ተሳታፊ አይሆኑም። የገዥዉ PDP ፓርቲ ብሄራዊ የፀጥታ ተጠሪ ፕሮፊሰር አደዋለ ኦላዲፖ እንደሚሉት ግን ሁኔታዉ ድንገተኛ ክስተት ቢሆንም፤ የፕሬዚዳንቱን የፖለቲካ ህይወት አያዉክም፤ «የፕሬዚዳንቱ የናይጀርያዉያኑን ፍላጎት የሚያሟሉ፤ ህዝቡ የሚፈልጋቸዉ አይነት ከሆነና በሳቸዉ እንዲመሩ የሚፈልግ ከሆነ፤ የዚህ ፓርቲ ቅንጅት የሳቸዉን የፖለቲካ እርምጃ የሚያስተጓጉል አይመስለኝም»
በናይጀርያዉ ፕሬዚደንት በጉድላክ ጆናታን እና በተቀናቃኞቻቸዉ መካከል ለመጭዉ የጎርጎረሳዊ 2015 ዓ,ም የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመቅረብ አለመቅረብ ክርክር እና ሽኩቻ የተጀመረዉ ከሁለት ዓመት በፊት በጎርጎረሳዉያኑ 2011 ዓ,ም ጉድላክ ጆናታን የፕሪዚዳንትነቱን በትረ ስልጣን ጨብጠዉ ቃለ ማኃላ እንደፈጸሙ ነዉ። እንደብዙዎች እምነት ሁሉ የሌጎስ ዩንቨርስቲ ተማሬዋ ናንሲ ሮበርትም፤ በናይጀርያ የሚገኙ ፖለቲከኞች በሀገሬቱ ከሚሰራዉ ሥራ ይልቅ በሀገሪቱ የሚመረጠዉ ፕሬዚዳንት ጉዳይ

ያሳስባቸዋል፤ ይላሉ ፤ «በጎርጎረሳዊዉ 2015 ዓ,ም ማን ፕሬዚዳንት ሆኖ ይመረጣል በሚል የሚደረገዉ ፍክክር እና ትግል ለማድረግ ግዜዉ አሁን ገና ነዉ ። እንደኔ እምነት አንድ ፕሬዚዳንትን ለመምረጥ ከአሁኑ ከመጨቃጨቅ ፤ ሰዎች ተመርጠዉ እዲያገለገሉ የታዘዙበትን ስራ በመቀጠል ናይጀርያ ወደፊት እንድትራመድ ማድረግ አለቸዉ»
ዋንኞቹ የናይጀርያ ፖለቲከኞች የሀገሪቱን በሚሊዮኞች ዶላር የሞቆጠር ዓመታዊ የድፍድፍ ነዳጅ ሽያጭ ሰብሳቢዎች ናቸዉ። በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቁት የናይጀርያ ዋንኞቹ የመንግስት ተጠሪዎች፤ በቀጣይ በከፍተኛ ፍጥነት አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በሩጫ ላይ ይገኛሉ።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic