በትግራይ የባቡር መስመር ዝርጋታ መሰረዙ ያስነሳዉ ቁጣ | ኢትዮጵያ | DW | 04.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በትግራይ የባቡር መስመር ዝርጋታ መሰረዙ ያስነሳዉ ቁጣ

የመቐለ ሽረህ ሃሞራ የባቡር መስመር ተቋርጦአል መባሉ በነዋሪዉ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ ተሰማ። አረና ትግራይ በበኩሉ የፊደራል መንግሥት ትግራይን በፖለቲካም በኤኮኖሚም እያገለላት ነዉ ብሎአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

«የአስቸኳይ አዋጁ ባይኖር በተቃዉሞ ትግራይ ትናጥ ነበር» አረና

 አድዋ ላይ ይገነባል የተባለዉን የፓን አፍሪቃ ዩንቨርስቲ የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከነዋሪዉ ጋር ባደጉት ዉይይት የባቡር ሥራ ግንባታዉ በኛ እድሜ የሚፈፀም አይደለም በማለታቸዉ ከሕዝብ ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረባቸዉ መሆኑም ተመልክቶአል። አረና ትግራይ በበኩሉ የፊደራል መንግሥት ትግራይን በፖለቲካም በኤኮኖሚም እያገለላት ነዉ ብሎአል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አገደን እንጂ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፍ ትናጥ ነበርም ሲል መግለፁን ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል። 


ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic