1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮ

ረቡዕ፣ ሰኔ 12 2016

ከበትግራይ ክልል በተለይም ከምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የተፈናቀሉ ዜጎች ዘንድሮ ከክረምት በፊት ወደቀዬአቸው እንደሚመለሱ ቃል ተገብቶላቸዋው የነበረ ቢሆንም ይህ አለመፈፀሙን ያነሳሉ። ከእንዳባጉና የተፈናቃዮች መጠልያ ያነጋገርናቸው ከምዕራብ ትግራይ ሑመራ የተፈናቀሉ የ6 ልጆች እናት የክረምት ወቅት በመግባቱ ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/4hGZF
በሽሬ የተፈናቃዮጭ መጠለያ ከአንድ ዓመት በፊት
በሽሬ የተፈናቃዮጭ መጠለያ ከአንድ ዓመት በፊትምስል Million Haileselasie/DW

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች ሮሮ

በትግራይ ክልል በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ለዲፕሎማቶች እና ዓለምአቀፍ ተቋማት እንዲሁም ሚድያዎች ባሰራጨው መግለጫው በትግራይ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ሁኔታ እየከፋ መሆኑ የገለፀ ሲሆን አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚያሻ አንስትዋል። ያነጋገርናቸው የፓርቲው የፖለቲካ ጉዳዮች ሐላፊ አቶ ኪሮስ ሃይለስላሴ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ፥ ለፖለቲካ ትርፍ ከሚገባው ቃል በዘለለ ፍቃደኝነት ይሁን ቁርጠኝነት የለውም ብለዋል። የትግራይ ተፈናቃዮች እስከሰኔ መጨረሻ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ ተባለ

በትግራይ የሚገኙ በተለይም ከምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የተፈናቀሉ ዜጎች ዘንድሮ ከክረምት በፊት ወደቀዬአቸው እንደሚመለሱ ቃል ተገብቶላቸዋው የነበረ ቢሆንም ይህ አለመፈፀሙን ያነሳሉ። ከእንዳባጉና የተፈናቃዮች መጠልያ ያነጋገርናቸው ከምዕራብ ትግራይ ሑመራ የተፈናቀሉ የስድስት ልጆች እናት መብራት ጥሩነህ፥ ከነበረው በርካታ እና የተወሳሰበ ችግር በተጨማሪ የክረምት ወቅት መግባቱ ተከትሎ ለከፋ ሁኔታ መዳረጋቸውን ይናገራሉ። ወይዘሮ መብራት "አራት ዓመት ያገለገለ የፕላስቲክ መጠለያ እንኳን አሁን ተቀዶ ዝናብ እና ፀሐይ እየተፈራረቁብን ነው" ይላሉ። ትግራይ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች እሮሮ

ተፈናቃዮች በሽሬና አቢአዲ የሚገኙ መጠለያዎች ከአንድ ዓመት በፊት
ተፈናቃዮች በሽሬና አቢአዲ የሚገኙ መጠለያዎች ከአንድ ዓመት በፊት ምስል Million Haileselasie/DW

ሌላው ተፈናቃይ ሙላት መኮንን በበኩላቸው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ወደ ቀዬአችሁ ትመለሳላችሁ ቢልም የተባለው እየተፈፀመ ባይሆንም አንዳንድ እርዳታ ሰጪ ተቋማት ያደርጉት የነበረ ድጋፍ እያቋረጡ በቅርቃር ላይ ገብተናል ይላሉ። 

ስለተፈናቃዮቹ ጉዳይ የተናገሩት የሳልሳይ ወያነ ትግራዩ አቶ ኪሮስ ኃይለስላሴ፥ እነዚህ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጣቸው ዓለምአቀፍ  ጫና እንደሚፈጥሩ፥ ለትላልቅ ሀገራት ፈተና ሆኖ ያለ የስደተኞች ጉዳይንም እንደሚያባብስ ገልፀዋል።

ከአንድ ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ህጻናት
ከአንድ ዓመት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ህጻናት ምስል IMAGO/ZUMA Wire

አቶ ኪሮስ "ተፈናቃዮች ካልተመለሱ ወደ ስደተኝነት ነው የሚቀየሩት። ከትግራይ ከኢትዮጵያ ወጥተው ሌላ አማራጭ ያያሉ። በተለይም ወጣቶቹ አሁን ከተፈናቃዮች መጠልያ እየለቀቁ ወደ የመን እንዲሁም በሱዳን በኩል ወደ ሊብያ እያመሩ ነው" ሲሉ አክለው ገልፀዋል። የትግራይ ተፈናቃዮች ቅሬታ

በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ