በትግራይ እየተካረረ ባለው ውዝግብ የመቐለ ነዋሪዎች አስተያየት
ረቡዕ፣ መስከረም 29 2017የትግራይ ሐይሎች በክልሉ ያሉ ፖለቲካዊ ሁኔታ በህዝብ ዘንድ መረባበሽ ፈጥሮ ይገኛል ሲሉ ገልጸው ነበር። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው መካረር ተከትሎ ስርዓት አልባነት እንዲፈጠር እንደማይፈቅዱ ያስታወቁ ሲሆን ሁኔታው በዝምታ አንመለከትም ሲሉም አቋማቸው ይፋ አድርገዋል።
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀመንበርነት የሚመሩት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን እንዳስታወቀው መስከረም 24 ካደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኃላ ህወሓትን ወክለው በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያሉባለስልጣናት ከሓላፊነታቸው እንዲወርዱ መወሰኑ ይፋ አድርጓል።
የህወሓት ክፋዩ መግለጫን ተከትሎ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባሰራጨው የፅሑፍ መግለጫ ደግሞ፣ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓቱ ቡድን ከዚህ በፊት የተለያዩ ማደናገርያዎች እያሰራጨ መቆየቱ በማንሳት፥ አሁን ላይ ግን በግልፅ "መፈንቅለ ስልጣን እንዳደረገ አውጇል" ብሏል። ይህም "ስርዓት አልባነት እንዲሰፍን ያለው ፍላጎት ማሳያ" ተደርጎ የሚታይ ነው ሲል ይገልፃል።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በዚህ "የጥፋት ሐይል" ብሎ የገለፀው አካል ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ያስታወቀ ሲሆን፥ ይህ ተከትሎ ለሚፈጠር ማንኛውም ጥፋት ደግሞ ተጠያቂው ይህ ቡድን እና አመራሩ ነው ትላንት አስታውቋል።
በሁለቱም ሃይሎች መካከል እየተካረረ የመጣው ውዝግብ ወደከፋ,ደረጃ እንዳይደርስ ስጋት እንዳላቸው የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ አስተያየቶቹን ያዳምጡ።
ሚልዮን ሃይለስላሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ