«በትርፍ ጊዜዬ በሬ አራጅ ነኝ» | ባህል | DW | 06.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

«በትርፍ ጊዜዬ በሬ አራጅ ነኝ»

ብዙ ወጣቶች ያልደፈሩትን ሥራ በተሰጥዎ እንደሚሰራ ይናገራል። ፋንቱ ያኖ። የ20 ዓመት ወጣት ነው። ከታናሽ ወንድሙ ጋ በአዲስ አበባ፤ ቂርቆስ አካባቢ ይኖራል። በሬ ማረድ ከጀመርኩ 3 ዓመት ሆነኝ ይላል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻውን ስላረደው በሬ በደንብ ያስታውሳል። በትርፍ ጊዜው በሬ ያርዳል። በተቀረ ጊዜው በረዳት ሰራተኛነት ያገለግላል። እንዲሁም ትልቅ ኃላፊነት አለበት። ታናሽ ወንድሙን ብቻውን ያስተዳድራል።

ፋንቱ የክርስትያኖች ቤት ነው የሚሰራው። በብዙ የፆም ወቅቶች እና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ወጣቱ በቂ ስራ ግን አያገኝም። ቋሚ ገቢ የማያስገኙ የበሬ ማረድ እና የቀን ስራዎች የፋንቱ ዋና መተዳደሪያዎች ናቸው። የአገኘውን ስራ ሳይመርጥ ይሰራል። ወጣቱ ምንም እንኳን ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ቢኖረውም ታናሽ ወንድሙንም ያስተዳድራል። የ13 ዓመት ታናሽ ወንድሙ ዘንድሮ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና (ሚኒስትሪ)ተፈትኖ ወደ 9ኛ ክፍል አልፏል። «እኔ ሰርቼ ስለማስተምረውም ተግቶ ይማራል፣ ጎበዝ ተማሪ ነው» ይላል ፋንቱ ስለወንድሙ ሲናገር። ታናሹ አሁን በክረምት ወራትም ይማራል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሬ በማረድ እና የቀን ስራዎችን በመስራት ራሱን እና ታናሽ ወንድሙን ስለሚያስተዳድረው የ 20 ዓመት ወጣት ፤ፋንቱ ያኖ ታሪክ መስማት ከፈለጉ የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic