በተገቢው መንገድ ሥራቸውን የማያከናውኑ የትምህርት ተቋማት | ኢትዮጵያ | DW | 22.08.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በተገቢው መንገድ ሥራቸውን የማያከናውኑ የትምህርት ተቋማት

በሕገወጥ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው የተገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ባልተፈቀደላቸው የትምህርት መስክ ላይ ተሰማርተው ተገኘተው እገዳ የተጣለባቸው 18 የግል ኮሌጆች የሀገሪቱ የትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደራቸውን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዛሬ አስታወቀ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

«በትምህርቱ ላይ አሉታዊ ጫና ማስከተላቸው ተገልጿል»

 ኤጀንሲው በዚህ ሕገወጥ እና የማይጠበቅ ሥራ ተሰማሩ ያላቸው ባሕር ዳር ፣ ጅማ ፣ ሀረማያ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች የተቋማቱን ሃብትና መምህራን በመጠቀም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ተገቢነት የጎደለው ሥራ ላይ ተሰማርተው መቆየታቸውን ፣ አሁን ግን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርን ክልከላ ተከትሎ 3ቱ ከድርጊታቸው
የተቆጠቡ ሲሆን ጅማ ዩኑቨርሲቲ ግን የሚኒስቴሩን አቅጣጫ ወደጎን በማለት አሁንም አስተምራለሁ እያለ ተማሪዎችንም እየመዘገበ እንደሚገኝ ኤጀንሲው ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። ዩኒቨርሲቲዎቹ መንግሥት የማያውቃቸውን ተማሪዎች እያስተማሩ ከፍተኛ ገንዘብ እየሰበሰቡ ነው የሚለው ኤጀንሲው በተለይ ጅማ ዩኑቨርሲቲ የሚያስከፍለው ገንዘብ የተጋነነና አዲስ አበባ ላይ አብሮት እየሠራ ያለውንም ተቋም እውቅና የተሰጠው ባለመሆኑ ተገቢው እርምጃ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንዲወሰድበት ተይቋል። በእነዚህ ተቋማት የተመረቁም ይሁን እየተማሩ ያሉት ተማሪዎች እጣን በተመለከተ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ወደፊት እርምጃ እንደሚወሰድና ግልጽም እንደሚደረግ ተገልጿል። ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች