«በተማርኩበት ት/ቤት አሁን አስተምራለሁ» ገብረ ስላሴ ለላጎ | ባህል | DW | 04.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

«በተማርኩበት ት/ቤት አሁን አስተምራለሁ» ገብረ ስላሴ ለላጎ

የዛሬው የወጣቶች ዓለም በሀዲያ ዞን የእንግሊዘኛ ቋንቋ አስተማሪ ከሆነ ወጣት ጋ ያስተዋውቀናል።

B Berta.jpg Liebe Kollege Die Bilder die ich gerade gebracht habe ist von mir. Es ist aus Äthiopien Eine Dorfgemeinschaft in der süd-äthiopischen Region Berta feiert die kulturelle und ethnische Vielfalt in ihrer Region. A local village community celebrates the cultural and ethnic variety in the Southern Ethiopian region of Berta. Liebe Grüße Azeb Tadesse Hahn

ገብረ ስላሴ ለላጎ ይባላል። በወላይታ ሶዶ ዮንቨርሲቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እና በጂኦግራፊ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል። ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ያስተምራል። አስተማሪ መሆንም ትልቅ ምኞቱ ነበር።

ገብረስላሴ አፉን የፈታው በሀዲኢሳ ቋንቋ ነው። ከዚህ ሌላ እንግሊዘኛ፣አማርኛ እና ከምባትኛ( ከምባቲሳ) ይናገራል። ወጣቱ የአስተማሪ እጥረት ሲኖር አልፎ አልፎ ጂኦግራፊ ያስተምራል። ተማሪዎቹ ትምህርቱ ካልገባቸው በሚገባቸው ቋንቋ አብራራላቸዋለሁ፤ አብዛኛውን ጊዜ ግን በእንግሊዘኛ ክፍለ ጊዜ እንግሊዘኛ ቋንቋ ነው የምጠቀመው ይላል። ገብረ ስላሴ።

የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጲያ ሲሄዱ መግባባት ስለሚቸግራቸው ከአስተርጓሚ ጋ መንቀሳቀስ ግድ እንደሚላቸው ይናገራሉ። ለዚህም ምክንያት የሚያደርጉት በብዙ አካባቢዎች ጥሩ እንግሊዘኛ ተናጋሪ አለማግኘታቸው ነው። ገብረስላሌ ግን በዚህ ሙሉ በሙሉ አይስማማም። ችግሩ "የድፍረት ማነስ ነው " ይላል።

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ት/ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ስለሆኑ እያንዳንዱ ተማሪ ቋንቋውን በንግግር የሚያዳብርበት መንገድ አዳጋች ነው። ገብረስላሴ እና ባልደረቦቹ ግን መፍትሄ አላቸው። የ 27 ዓመቱ ገብረ ስላሴ ራሱ ትምህርት ለማግኘት ምን ያህል እንደለፋ ሳይጠቅስ አላለፈም። ወጣቱ እንዴት አስተማሪ እንደሆነ እና ተሞክሮውን መስማት ከፈለጉ። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic