በተመድ የሩስያ አምባሳደር ዜና እረፍት | ዓለም | DW | 20.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

በተመድ የሩስያ አምባሳደር ዜና እረፍት

በተመ የሩስያዉ ቋሚ አምባሳደር ቪታሊ ቹርኪን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ 64 ዓመቱ ቹርኪን ከዚህ ዓለም የመለየታቸዉ ድንገተኛ ዜና የተሰማዉ ሰኞ ምሽት ላይ ነዉ። አምባሳደር ቹርኪን ከጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓ,ም ጀምሮ በተመድ የሩስያ ቋሚ አምባሳደር ሆነዉ አገልግለዋል።

 
ሞስኮ የሚገኘዉ የሩስያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቹርኪን 65ኛ የልደት በዓላቸዉን ለማክበር አንድ ቀን ሲቀራቸዉ በድንገት ማረፋቸዉን ከማሳወቅ በስተቀር በዝርዝር የገለፀዉ ነገር የለም። ባለፈዉ ጥቅምት ወር የዉስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ግርማ አስመሮም በድንገት ማረፋቸዉ ይታወሳል፡፡ የ 68 ዓመቱ አምባሳደር ግርማ አስመሮም ለስራ ወደ ኒው ዮርክ ከመምጣታቸዉ በፊት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት፣ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ የኤርትራ አምባሣደር ሆነው መስራታቸዉ ይታወሳል። 
 
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ