በቩርስቡርግ የባቡር ላይ ጥቃት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 19.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

በቩርስቡርግ የባቡር ላይ ጥቃት

በደቡብ ጀርመን፣ በባቫሪያ ግዛት በምትገኘው በቩርስቡርግ እና በትሮይሽትሊንገን ከተሞች መካከል ሲጓዝ በነበረ አንድ ያካባቢ የመንገደኞች ማመላለሺያ ባቡር ላይ ትናንት ምሽት አንድ ወጣት በመጥረቢያ እና በጩቤ በጣለው ጥቃት በርካቶች ቆስለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:39

ጥቃት በቩርስቡርግ

ከአፍጋኒስታን የመጣ ተገን ጠያቂ ነው የተባለው አጥቂ በፖሊሶች መገደሉን የባቫሪያ ሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ጥቃቱ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዘ መሆን አለመሆኑ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ያካባቢው ፀጥታ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ባቡር ውስጥ ስለተጣለው ጥቃት፣ ስለ አጥቂው እና ስለምርመራው በርሊን የሚገኘውን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር። በመጀመሪያም የጠየቅሁት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic