በቦይንግ ላይ ክስ መመስረቱ | ኢትዮጵያ | DW | 03.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በቦይንግ ላይ ክስ መመስረቱ

ባለፈው ጥር 17 ,2002 ዓ.ም ከሊባኖስ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ የሞቱ ተሳፋሪዎች ቤተሰቦች በቦይንግ ላይ ክስ መመሰረታቸው ተገልጿል ።

default

በነዚሁ ቤተሰቦችም ክሱን የመሰረተው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የአቭየሽን ጉዳዮችን በማስፈፀም ከፍተኛ ዕውቅና ያለው ሬቤክ የተሰኘው የህግ አገልግሎት ድርጅት ነው ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለዶይቼቬለ የአማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ምልልስ ክስ የመሰረቱት ሁለት ኢትዮጵያውያንና አንድ ሊባኖሳዊ መሆናቸውን ተናግረዋል ። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ