በብሪታንያ ከተሞች የቀጠለዉ ዓመጽ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

በብሪታንያ ከተሞች የቀጠለዉ ዓመጽ

በለንደን ከተማ ባለፈው ቅዳሜ የተጀመረው የወጣቶች ተቃውሞ እና ዓመጽ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

ሁከቱ ወደ ሌሎች በርሚንግሀም፡ ሊቨርፑል፡ ብሪስቶል እና ኖቲንግሀም የተስፋፋ ሲሆን፡ በለንደን የንግድ መደብሮች፡ መኖሪያ ቤቶች ተሽከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል። ካለፈቃድ መሳሪያ ይዞ የተገኘ አንድ የሀያ ዘጠኝ ዓመት ወጣት ባለፈው ቅዳሜ በፖሊስ ከተገደለ በኋላ የተነሳው ሁከት ተባብሶ የቀጠለበት ሁኔታ ያሳሰባቸው እና ዕረፍታቸውን አቋር’ጠው ወደ ለንደን የተመለሱት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካምሮን ሁከቱን አውግዘዋል።

ድልነሳ ጌታነህ

አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic