1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤይሩቱ ፍንዳታ አንድ የጀርመን ዲፕሎማት ሞቱ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2012

መዲና ቤይሩት አሞኒየም ናይትሬት የተባለ የእሳት ማቀጣጠያ ኬሚካል ባስከተለዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ አንዲት የጀርመን ኤንባሴ ሰራተኛ ቤታቸዉ ዉስጥ መሞታቸዉ ተገለፀ። «የፈራነዉ ነገር ደርሶአል» ሲሉ ጀርመናዊትዋ ዲፕሎማት በፍንዳታዉ ቤታቸዉ ዉስጥ ሞተዉ መገኘታቸዉን  የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3gYdN
Deutschland Berlin Auswärtiges Amt
ምስል Imago/STPP

መዲና ቤይሩት አሞኒየም ናይትሬት የተባለ የእሳት ማቀጣጠያ ኬሚካል ባስከተለዉ ሁለት ከፍተኛ ፍንዳታ አንዲት የጀርመን ኤንባሴ ሰራተኛ ቤታቸዉ ዉስጥ መሞታቸዉ ተገለፀ። «የፈራነዉ ነገር ደርሶአል» ሲሉ ጀርመናዊትዋ ዲፕሎማት በፍንዳታዉ ቤታቸዉ ዉስጥ ሞተዉ መገኘታቸዉን  የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ አስታዉቀዋል። ማስ ለሟች ቤተሰቦች ወዳጅ ጓደኞች ብሎም በጀርመናዉያን ስም የተሰማቸዉን ሃዘን ገልፀዋል። ከትናንት በስትያ ምሽት ላይ በሊባኖስ መዲና ቤይሩት በተከሰተ ሁለት እጅግ ከፍተኛ ፍንዳት ቢያንስ 137 ሰዎች ሞተዋል፤ ወደ 5000 ሺህ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፍንዳታዉ ምክንያት ይሙቱ ይኑሩ ያልታወቀ ብዙ ሰዎች አሁንም እየተፈለጉ ነዉ።   

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ