በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኮሮና ምርመራ ተጀመረ  | ጤና እና አካባቢ | DW | 20.05.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኮሮና ምርመራ ተጀመረ 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሮና  ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።የክልሉ የጤና ቢሮ እንደገለፀው  ምርመራውን የጀመረው በሰዓት እስከ 94 ናሙናዎችን በቀን ደግሞ 500 ሰዎችን መመርመር በሚያስችል  ማሽን ን ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የኮሮና ተዋህሲ ምርመራ ተጀመረ

 

 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሮና  ቫይረስ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።የክልሉ የጤና ቢሮ እንደገለፀው  ምርመራውን የጀመረው በሰዓት እስከ 94 ናሙናዎችን በቀን ደግሞ 500 ሰዎችን መመርመር በሚያስችል  ማሽን ን ነው።ክልሉ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በትናንትናዉ ዕለት ነው የምርመራ ስራዉን በይፋ የጀመረ ሲሆን እስካሁን 13 ናሙናዎች ላይ ምርመራ አድርጓል። 

በሰዓት እስከ 94 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችለው ማሽን ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆሶፒታል እና አጋዥ ቁሳቆሶችን ደግሞ ከኢትየጵያ ኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በተገኘ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዋጮ ዋቡልቾ አመልክተዋል፡፡ በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ስራ የጀመረው የኮሮና ተዋሐሲ መመረመሪያ ማሽኑ  ትናንት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሐሰን  በይፋ ተመርቆ ስራ መጀመሩንም ሓላፈው ተናግረዋል፡፡ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል  የላብራቶሪ ምርምራ ሀላፊ አቶ ጋርቢ ሎላሳ በበኩላቸው በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ስራው መጀመሩንና እስካሁን 13 ናሙናዎችን መመርመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በርካታ የስዴኞች መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙና ከሱዳንም በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ክልል በመሆኑ፤  የኮሮና ተዋሐሲን ለመመረመር የሚስችል ማሽን  በክልሉ በቶሎ  ስራ እንዲጀምር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዋጮ ዋቡልቾ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ፣ባህርዳር እና ነቀምት  በመላክ ውጤቶችን ሲገልጹ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መጀመሩ ጊዜና ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ በበሚገኙ የካመሺ፣አሶሳ እና መተከል ዞኖች በተዘጋጁ  የተለያዩ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉት የኮሮና ቫረስ ህሙማንን በቅርበት አገልግሎት ለመስጠትና ወቅታዊ ክልላዊ መረጃዎችን ለጤና ሚኒስቴር ለማድረስም ያስችላል ብለዋል፡፡ ቫይረሱ በኢትጵያ ከተገኙ ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬው ዕለት  በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል 478 ሰዎች ጊዜያዊ ማቆያ የገቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል 130 የሚደርሱት ሱዳናዊያን መሆናውቸውን አመልክቷል፡፡ በተደረገላቸው ክትትልም ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ወደ መጡበት አካባቢ የተመለሱም መኖራቸውን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ሪጅናል ላብራቶሪ ምርምር ተቋም ኃለፊ የሖኑት  አቶ ጋርቢ ሎላሳ  በበኩላቸው በክልሉ ስራ የጀመረው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማሽን በቀን እስከ 500 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም እንዳለው  የገለጹ ሲሆን ናሙናዎችን የመመሪመር  ተግባር በክልሉ በይፋ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና ሰልጋ አሎ ከተባሉ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ናሙናዎች የተወሰደ ሲሆን ውጤቱም በኢትዩጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲውት በኩል የሚገለጽ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የጤና ሚስቴር ባለፈው ሳምንት ሐሙስ  ባወጣው  መግለጫ  ከቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዌ ወረዳ ለይቶ ማቆያ የነበሩ ሁለት ሰዎች  የኮሮና ተዋህሲ እንደተገኘባቸው  ይፋ አድርጓል፡፡  በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሀል በተባለው ድንበር በኩል ሱዳን ቆይቶ የተመለሱ እንደነበሩም ታውቋል፡፡ አልማሀል በተባለው አካባቢ በርካታ ሰዎች  ከሱዳን ወደ ኢትዩጵያ እንዲሁም ከኢትዩጵም ወደ ሱዳን የሚዘዋወሩበት በር ሲሆን ከአንድ ወር በፊትም 35 የሚደርሱ ሰዎች በዚው አካባቢ ወደ ኢትዩጵያ ሲገቡ ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀዩ መደረጋቸውን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ፀሀይ ጫኔ

እሸቴ በቀለ

 

Audios and videos on the topic