በቤንሻንጉል ጉሙዝ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ | ኢትዮጵያ | DW | 29.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተቀሰቀሰው ግጭት እንደገና አገርሽቶ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የአማራ ክልል ቃል አቃባይ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ወደ ብሔር ተኮር ተቀየረ ባሉት ግጭት 17 ሰዎች መሞታቸውን ዛሬ ለጀርመን ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:20

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት የተቀሰቀሰው በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አይሲካ ቀበሌ ባለፈው ሐሙስ ነበር። በቀበሌው ባሉ ጫኝ እና አውራጆች ግለሰቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ወደ ብሔር ግጭት መቀየሩን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። 

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አዲጎ አምሳያ ትላንት እስከ ምሽት ድረስ ስምንት መሞታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ አዲጎ በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ማጣራት እያደረጉ እንደሆነ ቢገልጹም የአማራ ክልል ቃል አቃባይ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ግን በግጭቱ 17 ሰዎች መሞታቸውን ለጀርመን ዜና አገልግሎት ዛሬተናግረዋል። 

ለግጭቱ መንስኤ የሆነው በአማራ እና ጉሙዝ ብሔር ተወላጆች መካከል በዳንጉር ወረዳ የተፈጠረ የግል ጸብ ወደ ብሔር ተኮር ግጭት መቀየሩ እንደሆነ አቶ አሰማኸኝ አስረድተዋል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ የብሔር ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንደነበሩ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከትናንት ከሰዓት ወዲህ መሻሻል አሳይቷል ቢሉም ነዋሪዎች ግን በአካባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን ለዶይቼ ቬለ የአሶሳ ተናግረዋል።  

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ነጋሳ ደሳለኝ

ተስፋለም ወልደየስ

እሸቴ በቀለ 

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች