በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሁለት ወረዳዎች ሃያ ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ | ኢትዮጵያ | DW | 01.08.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሁለት ወረዳዎች ሃያ ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በወረዳው ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ውስጥ እስከ ባለፈው ረቡዕ ድረስ የመተከል ዞን የኦሮሞ ተወላጆችን  በአባ ገዳነት ሲመሩ የነበሩና ሰብሳቢ የነበሩ አቶ ዳባሎ ሂካን ጨምሮ ሌሎችም ሰዎች ከኦነግ ሸነ ጋር ግንኙነት አላቹ  ተብለው መታሰራቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ገልጸዋል፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:49

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰዎች እየታሰሩ ነው

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢና ቡሌን በተባሉ  ወረዳዎች ውስጥ 20 የሚደርሱ   ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በወረዳው ጋሌሳ በተባለ ቀበሌ ውስጥ እስከ ባለፈው ረቡዕ ድረስ የመተከል ዞን የኦሮሞ ተወላጆችን  በአባ ገዳነት ሲመሩ የነበሩና ሰብሳቢ የነበሩ አቶ ዳባሎ ሂካን ጨምሮ ሌሎችም ሰዎች ከኦነግ ሸነ ጋር ግንኙነት አላቹ  ተብለው መታሰራቸውን የታሳሪ ቤተሰቦች ገልጸዋል፡፡ ከታሰሩት መካከል የሆቴል ባለንብረቶችና በሌሎች የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ይገኙበታል ብለዋል፡፡ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ  በድባጢ እና ቡሌን ወረዳዎች የህዝቡን ሰላም የሚያውኩ የኦነግ ሸኔ  ጋር ግንኙነት ያላቸው  መሳሪያ ያስቀመጡ፣ የምግብ ድጋፍ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል፡፡

በመተከል ዞን ድባጢ እና ቡሌን  ወረዳዎች   በተለየዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከባለፈው እሁድ አንስቶ ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኑነት አላቹ ተብለው በርካታ ሰዎች መታሰራውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡  በድባጢ ወረዳ ጋለሳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እና የቤተሰባቸው አባል መታሰሩን የገለጹት አቶ ዋዩ ለሚ ከታሰሩት ሰዎች መካከል አቶ ዳባሎ ሂካ የተባሉ በዞኑ የኦሮሞ ተወላጆችን በአባዳገዳነት ሲመሩ የነበሩና ከዚህ በፊት የጋለሳ ቀበሌን የወረዳ እንሁን ጥያቄንም ሲያስተባብሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በጋለሳ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከስድስት ወራት በፊት ጽ/ቤት ከፍተው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ዋዩ ገለጻም «ከታሰሩት መካከል ነጋዴዎች እና አርሶ አደሮችም ይገኙበታል»፡፡

በድባጢ ወረዳ ቆርቃ ቀበለ፣ጋለሳ እና ሶምቦ ስሬ በተባሉ እንዲሁም  ከቡለን ወረዳ  ድገሞ በኩጅ እና ጭላንቆ  ከተባሉ አካባቢዎች 20 የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን ሌላው ከቡሌን ወረዳ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ «ሰዎቹ  ከየስራ ቦታቸው  በጸጥታ ሀይሎች ተይዘው መታሰራቸውን እንጂ በወቅቱ ለምን እንደተፈለጉ እና በምን ወንጀል እንደተረጠሩ አልታወቀም» ብለዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ  በስልክ እንደተናገሩት «በተጠቀሱት አካባቢዎች የነዋሪውን ሰላም የሚያውኩ አካላት እየተሰንቀሳቀሱ የሚገኙበት ስፍራ መሆኑ የተደረሰበት እና በጥናት የተለዩ አካባቢዎች ናቸው »ብለዋል፡፡ «ታሰሩ የተባሉ ሰዎችም መረጃ ያቀበሉና በተለያዩ መንገዶች ለታጣቂዎችን ድጋፍ አድርገዋል  ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች መሆናቸውንና ተለይተው መታሰራውን »ገልጸዋል፡፡ « ነገር ግን በዞኑ ውስጥ ታስረዋል ስለ ተባሉ አባ ገዳዎች ጉዳይ  የደረሰን መረጃ የለም » ብለዋል፡፡    

የመተከል ዞንን ከሌሎች ክልሎች ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ከዚህ በፊትም ነዋሪው ለረዥም ጊዜ ለሰላም እጦት ተጋልጦ እንደነበር የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል፡፡ «ወደ ቀየአቸው የተመለሱ ዜጎች መደበኛ የእርሻ ተግባራቸውን እንዲከናውኑና  ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዩች ላይ ጥናት በማድረግ ችግሮችን እንዳይፈጠሩ ለማድረግ ጥረት አያደረግን እንገኛለን» ብለዋል፡፡  

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

Audios and videos on the topic