በቤኒሻንጉል ክልል የተዘጉ ት/ቤቶች እየከፈቱ ነዉ ተባለ | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቤኒሻንጉል ክልል የተዘጉ ት/ቤቶች እየከፈቱ ነዉ ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ባለፉት ስድስት ወራት 19 በሚሆኑ ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂዴት ተቋርጦው እንደ ነበር የወረዳው ት/ት ጽ/ ቤት አስታውቋል። ተቋርጠው የነበረውን የመማር ማስተማር ሂዴት ሙሉ ለሙሉ ለማስጀመርም ከጥር ወር አጋማሽ ጀምሮ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሎአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:33

በ19 ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ ነበር

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ባለፉት ስድስት ወራት 19 በሚሆኑ ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ሂዴት ተቋርተው እንደ ነበር የወረዳው ት/ት ጽ/ ቤት አስታውቋል። ከዚህ በፊት በአካባቢው ተፈጥረው  በነበረ የሰላም መደፍረስ ምክንያት ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ አልነበሩም፣ በርካታ መምህራንም ሸሽተው ነበር ይላል ከጽ/ ቤቱ ያገኘነው መረጃ፡፡ ተቋርጠው የነበረውን የመማር ማስተማር ሂዴት ሙሉ ለሙሉ ለማስጀመርም  ከጥር ወር አጋማሽ  ጀምሮ ጥረት እየተደረገ ነው ሲሉ የማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ት/ጽ/ቤት  ሀላፊ አቶ ያዕቆብ ሙስጠፋ ለዲዳቢሊው በስልክ ተናግረዋል፡፡በወረዳው ከሚገኙት 46 ት/ቤቶች 19ኙ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ያዕቆብ እስካሁን ቀይባና ኩሳየ የተባሉ አንደኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ስራ አለመጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡ የተማሪዎችን ጫና ለመቀነስና ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢው የሰላም ሁኔታ ዘላቂ እንዲሆን ከነዋሪዎችና ኮማንድፖስቱ ጋር በመሆን ውይይቶች እየተደረጉ እንደሆነም አስረድቷል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ት/ት ቢሮ በበኩሉ የሚስተዋሉትን የመምህራን እጥረትን ለመፍታት ከጽ/ቤቱ ጋር እየሰራው ነው ብለዋል፡፡ የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይረክተር አቶ ምትኩ ዘነበ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ከትምህርት ሚኒስተር ጋር በመነጋገር ውሳኔዎች ይሰጣሉ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜበወረዳው 42 በሚሆኑ ት/ቤቶች ከ10ሺ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሆኑ ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ነጋሳ ደሳለኝ

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic