በቤኒሻንጉልዋ ዳንጉር 57 ሰዎች ተገደሉ  | ኢትዮጵያ | DW | 26.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በቤኒሻንጉልዋ ዳንጉር 57 ሰዎች ተገደሉ 

የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል። የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውም ገልጸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:51

በዳንጉር 57 ሰዎች ተገደሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባንጂ በተባለ ስፍራ የታጠቁ ኃይሎች ባለፈው እሁድ አደረሱት በተባለ ጥቃት የ57 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ጃራ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከመካከላቸው በተኙበት በእሳት ተቃጥለው የሞቱም ይገኙበታል።የተቀሩት ደግሞ በጥይት ተመተው መገደላቸውን  17 ሰዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። 44 ቤቶችም መቃጠላቸውን ተናግረዋል። የአሶሳው ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ዘገባ አለው።

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic