በባለስልጣናት የዉጭ ጉዞ ላይ ያረፈው ገደብ | ኢትዮጵያ | DW | 30.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በባለስልጣናት የዉጭ ጉዞ ላይ ያረፈው ገደብ

የኢትዮጵያ መንግስት አገሪቱን ያጋጠማትን የዉጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቆጣጠር ባለስልጣናት የሚያደርጉትን የዉጭ ጉዞ በቂ ምክንያት ከሌለዉ መከልከሉ ይታወሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:19

የዉጭ ጉዞ ገደብ

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቅርቡ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር ባደረጉት ዉይይት አገሪቱን ያጋጠመዉን የዉጭ ምንዛሪ «ብክነት» ለመከላከል በመንግስት በኩል ርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ካሉ ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ የገንዘብና እኮኖሚክ ትብብር ሚንስቴር ባወጣው የዉስጥ መመሪያ ይህንን ስራ ላይ ለማዋል  አጠናክሮ እንደሚሰራ  የሚንስቴሩ የሕዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሃጅ እብሳ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የባለስልጣናት የዉጭ ጉዞን መገደብ የዉጭ ምንዛሪ ብክነት ይቆጣጠራል ያሉት እንደ ምሳሌነት የተነሳ ነዉ እንጅ የአጋርቱ የዉጭ ምንዛር እጥረት ይቀረፋል ማለት እንዳለሆነ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳምሶን ገብረስላሴ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ። «ሊማታዊ» ያሊሆነ ወጭዎች ወይም የወጭ ምንዛር ብክነት አለ የምሉት ባለሙያዉ አንዱም ተጠያቂ መንግስት መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ከአቶ ሳምሶን ሃሳብ ጋር የምስማሙት የሕዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሃጅ እብሳ የዉጭ ሚንዛሪ እጥረትን ችግር ለማቃለል ከተፈለገ የገቢና የወጭ ንግድን ማጣጣም፤ ብሎም አገሪቱ ወደ ዉጭ ገበያ የምትልከዉ ቡናን የመሳሰሉ ምርቶችን ጥራትና ብዛት ማሻሻል ዘላቅ መፍትሔ እንደሚሆን ያምናሉ። ባለፈዉ ዓመት በወጭ ቅነሳ ላይ የወጣዉ መመሪያ  አጥጋቢ ምክንያት የሌላቸውን የባለስልጣናትን ጉዞ መከልከልን ጨምሮ ሌሎች 19 ነጥቦችን እንደሚገድብም ተገልጿል።

በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በዶይቼ ቬሌ ፌስቡክና ዋትስአፕ ከተወያዩት አንዳንዶቹ እንዳሉት፣  «ባለሥልጣናት ለሥራ ሣይሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመዝናናት የመንግሥትና የህዝብን ገንዘብ እያባከኑ» ስለሆነ የመንግስት ርምጃ መልካም ነው፣ ሌሎች ደግሞ  «ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ዓይነት በመሆኑ እና ታዛዦቹ ከአዛዦቹ በላይ ተደራጅተዋል ብለው ስለሚያስቡ የርምጃውን ውጤታማነት እንደሚጠራጠሩ ገልጸዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic