በቢንላደን አገዳደል ሁኔታ ፓኪስታን በዩኤስ ላይ ያነሳችዉ ቁጣ | ዓለም | DW | 14.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በቢንላደን አገዳደል ሁኔታ ፓኪስታን በዩኤስ ላይ ያነሳችዉ ቁጣ

ዪናይትድ ስቴትስ በልዪ ኮማንድ የአልቃይዳዉን መሪ ኦሳማ ቢላደንን ለመግድል የወሰደችዉን እርምጃ ፓኪስታን ነቀፈች።

default

ኢስላማባድ ቢን ላደንን ለመግደል በተደረገዉ እርምጃ ደስተኛ አይደለችም

በፓኪስታን ቢላደን ከተገደሉ ከሁለት ሳምንት በዃላ የኢስላማባድ መንግስት ከዋሽንግተን ጋር የሚደርገዉን ግንኙነት ማጣራትም እንደሚፈልግ አስታዉቋል። የፓኪስታን ፓርላማ አባላት የአሜሪካ ልዪ ኮማንዶ ኦሳማ-ቢን-ላደንን ለመግደል የወሰደዉ እርምጃ የአገሪቱን ሉአላዊነት የሚጻረር ነበር ሲሉ ኮንነዋል። የፓርላማ አባላቱ በጋራ ባሳለፉት ዉሳኔ ከሁለት ሳምንት በፊት የአልቃይዳዉ መሪ አቦታባድ ለመግደል የተፈጸመዉ ድርጊት በአንድ ነጻ አጣሪ ኮሚሽን መመርመር አለበት። በሌላ በኩል ፓኪስታን እስላም አክራሪነትን ለመታገል በቂ እንቅስቃሴ አላደረገችም ሲል የሚወቅሰዉ የዋሽንግተኑ መንግስት በበኩሉ ኦሳማ-ቢን-ላደን ፓኪስታን ዉስጥ እንዴት ረጅም ግዜ ሊሸሸጉ እንደበቁ ለማጣራት የራሱን ምርመራ እያካሄደ ነዉ።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን