በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ እንዲጣራ መጠየቁ | ዓለም | DW | 05.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ እንዲጣራ መጠየቁ

ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:53
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:53 ደቂቃ

በቢሾፍቱ የሞቱት ጉዳይ እንዲጣራ መጠየቁ

ባለፈው እሁድ በቢሸፍቱ በእሬቻ በዓል የሞቱት ሰዎች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ሽትራስቡርግ ፈረንሳይ በመካሄድ ላይ ባለው የአውሮጳ ፓርላማ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተጠየቀ ። ጥያቄውን ያቀረቡት በ 1997 የተካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮጳ ህብረት ታዛቢ እና በአውሮጳ ፓርላማ የፖርቱጋል ሶሻሊስት ፓርቲ ተወካይ አና ጎሜሽ ናቸው ። ትናንት በጉባኤው ሂደት ጣልቃ በመግባት ጥያቄውን ያቀረቡት ጎሜሽ የአውሮጳ ህብረት በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ ከማለፍ እንዲቆጠብም አሳስበዋል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic