በበርሊን ሙዚየም ያሉ አጽሞች ጉዳይ እያሟገተ ነው | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

በበርሊን ሙዚየም ያሉ አጽሞች ጉዳይ እያሟገተ ነው

በጀርመን መዲና በርሊን ባለው ብሔራዊ ሙዚየም በሺህዎች የሚቆጠሩ ከአፍሪካ የመጡ ቅሪተ አካላት ጭምር ይገኛሉ። “አጽሞቹ ወደመጡበት ወደ አህጉራቸው ይመለሱ” የሚለው ጥያቄ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡ ጠያቂዎቹ “አጽሞቹ በክብር ማረፍ አለባቸው” ሲሉ ይሞግታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28

በሙዚየም ያሉት አጽሞች በክብር ማረፍ ይገባቸዋል ተብሏል

በበርሊኑ ብሔራዊ ሙዚየም ከአፍሪካ የመጡ በርካታ ቁሳቁሶች ይገኛሉ፡፡ በወመዘክሩ ያሉት ስዕሎች እና የእጅ ስራዎች፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ምንጣፎች ወይም እንደሚባለው ወንበሮች እና አንካሴዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ከአፍሪካ የመጡ ቅሪተ አካላት ጭምር እንጂ፡፡ በጀርመን መዲና “ አጽሞቹ ወደመጡበት ወደ አህጉራቸው ይመለሱ” የሚለው ጥያቄ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡ ቀጣዩ የዳንኤል ፔልስ ዘገባ “አጽሞቹ በክብር ማረፍ አለባቸው” የሚለውን ሙግት እና ምላሹን ያስቃኛል፡፡ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ያጠናቀረውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡  

ይልማ ኃይለሚካኤል/ዳንኤል ፔልስ

ተስፋለም ወልደየስ

ሂሩት መለሰ 

Audios and videos on the topic