በሽብር ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑ | ኢትዮጵያ | DW | 20.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

በሽብር ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑ

በፌደራል አቃቤ ሕግ በአሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸዉ የታሰሩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ«አንድነት» የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተጠርጣሪዎች በነጻ እንዲሰናበቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ወሰነ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:57 ደቂቃ

በሽብር ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑ


ነጻ እንዲሰናበቱ ከተወሰነላቸዉ ከነዚሁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል አንዱ ዛሬ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተላልፏል ። ሶስቱ ግን ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተላለፈባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ነው የተወሰነው። በሽብርተኝነት ክስ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ግድም ታስረው ዛሬ በነፃ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌዉና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፤ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ናቸው።

በነጻ እንዲሰናበቱ የተወሰነውም በቀረበባቸዉን የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሪ ባለፈ ተሳትፎአቸዉን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በዉሳኔዉ ማስታወቁ ተገልጿል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታሳሪዎቹ ከእስር ቤት አልወጡም። የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት እንደሚሉት ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲወጡ ወስኖአል፤ ይወጣሉ የሚል ተስፋ አለን።

Gericht Gesetz Jura Hammer Waageየፓርቲያችን ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብረሃ ደስታ የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ፍፁም እምነት የለንም ያሉት አቶ ገብሩ አስራት በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዉ የታሰሩ ሁሉ እንዲለቀቁም ጠይቀዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸዉ አንድ ሰዉ ይህን ያህል ጊዜ ለምን ይታሰራል ሲሉ ጠይቀዋል። እንዲለቀቁ የተፈረደላቸዉ እስረኞች እስር ላይ ሳሉ ችሎት በመድፈር በሚል ተከሰዉ ስለነበር ይዉጡ አይዉጡ ገና አልታወቀም ሲሉ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic