በሸካ ደን ላይ የደረሰዉ የእሳት ጉዳት  | ኢትዮጵያ | DW | 27.03.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

በሸካ ደን ላይ የደረሰዉ የእሳት ጉዳት 

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን  የሚገኘዉ የሻካ ደን በዓለም የትምሕርት፤ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) በቅርስነት የተመዘገበ ጥብቅ ደን ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00

የሸካ ደን መቃጠሉ

አሁን በእሳት መንደድ ከጀመረ ሁለተኛ ሳምንቱን ማገባደዱን የደቡብ ክልል የደን እና የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ቃቃቦ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። 
የሸካ ጥብቅ ደን ባአጠቃላይ 238,750 ሔካታር መሬት እንደሚሸፍን  መረጃዎች ያመለክታሉ። እሳቱ እስካሁን  200 ሔክታር የሚሸፍን ደን ማጋየቱን ኃላፊዉ ይናገራሉ።

የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ለማ መለሰ ግን እሳቱን በአብዛኛዉ አከባቢ መቆጣጠር ቢቻልም ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ግን አልተቻለም ይላሉ። የቃጠሎዉ መነሻ «ሰደድ እሳት» መሆኑን አቶ ለማ ገልፀዋል።

የሸካ ደን በሶስት ቦታዎች እንደሚካፈል የሚናገሩት በመልካ-ኢትዮጵያ የሸካ ፕሮጄክት አስተባባር አቶ አዱኛ ሳዌኖ እነሱም ጥብቅ ወይም መሠረት /ኮር/ ደን፣ መከለያ /ባፈር/ ደን እንድሁም መሸጋገሪያ /ትራንዝሽናል/ ደን መሆኑን ገልፀዋል። የጥብቅ ዉይም የኮር ደን ዳግም በሰባት ቦታዎች ተካፍለዉ ሲገኙ ከከሰባቱ ዉስጥ አንዱን እሳቱ ማጥቃቱንም አቶ አዱኛ አክሎበታል።

በደኑ ዙርያ ለኢንቬስትመንት የተዘጋጀዉ መሬት 107,000 ሔክታር መሬት መሆኑን የሚናገሩት የአከባቢ ጥበቃና ደን ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አባዛኛዉ ባለሐብቶች የተሰማሩትም በቡና ኢንቬስትሜንት መሆኑን አክሎበታል። አቶ ለማ በበኩላቸዉ እሳቱ በክልሉ ቱርዝምና እንቬስትሜንት ላይ ብዙም ለአደጋ እንዳላስከተለ ገልፀዋል።

በሸካ ደን አከባቢ በቡና ላይ ኢንቬስት የሚያደርጉ የአገር ዉስጥና የዉጭ ኢንቬስቴሮች ይገኙበታል። ከነዚሕም የአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ንብረት መሆኑ የሚነገረዉ በ1,500 ሔክታር ላይ ያረፈዉ የቡና ተክል ሲሆን ከዉጭዎቹ ደግሞ  ኦሪጂናል ፉድ የተሰኘዉ የጀርመን ኩባንያ  ይገኝበታል።

የሸካ ዞን በደቡብ ከቤንች ማጂ ዞን፤ በምሥራቅ ከካፋ፣ በምዕራብ ከጋምቤላ ክልል፣  እና በስተ ደቡብ ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ይዋሰናል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic